በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በአማራ ክልል እሁድ ዕለት ሦስት ወጣቶች መገደላቸው ቤተሰቦቻቸውና ነዋሪዎች ገለጹ


አቶ ዘውዱ ገብረማርያም እና አቶ ሙላው ከበደ የተባሉ ሁለት ግለሰቦች በመተማ አቶ ባህሩ ይታየው የተባለ ደግሞ በጎንደር ከተማ እሁድ ዕለት መገደላቸውን ነዋሪዎችና ቤትሰብ ለአሜሪካ ድምጽ ገልፀዋል። የክልሉ የመንግሥት ኮሙዩኒኬሽን ዳይሬክተር ተገደሉ ስለተባሉት ወጣቶች ለጊዜው ከአካባቢው ርቀው ስለሚገኙ "መረጃ የለኝም" ብለዋል።

በአማራ ክልል በመተማ ሁለት የወልቃይት ተወላጆች፣ በጎንደር ከተማ ደግሞ አንድ የማክሰኝት ከተማ ተወላጅ በድምሩ ሦስት ወጣቶች ታኅሣሥ 9/2009 በፀጥታ ኃይሎች መገደላቸውንና በትናንትናው ዕለት የቀብር ሥነ- ስርዓታቸው መፈጸሙን ቤተሰብና ነዋሪዎች ለአሜሪካ ድምጽ ገለጹ።

ነዋሪዎቹ “በክልሉ ሰዎች ይገደላሉ፣ ይታሰራሉ አንዳንዶቹ የደረሱበት አይታወቅም። የክልሉ መንግሥት ለዜጎቹ ምንም የሚያደርገው ጥበቃ የለም ” ይላሉ።

የክልሉ የመንግሥት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ዋና ዳይሬክተር አቶ ንጉሡ ጥላሁን በበኩላቸው መንግስት ለዜጎቹ ጥበቃ እንደሚያደርግ ገልጸው ተገደሉ ስለተባሉት ወጣቶች ለጊዜው ከአካባቢው ርቀው ስለሚገኙ "መረጃ የለኝም" ብለዋል።

ጽዮን ግርማ ያጠናቀረችውን ዘገባ ለማድመጥ የተያያዘውን የድምጽ ፋይል ያድምጡ።

በአማራ ክልል እሁድ ዕለት ሦስት ወጣቶች መገደላቸው ቤተሰቦቻቸውና ነዋሪዎች ገለጹ
please wait

No media source currently available

0:00 0:07:34 0:00

XS
SM
MD
LG