እስኪመለስ የቀጠለ ይመስላል፤ ሁነኛ መልስ ፍለጋው። የአገር ጉዳይ ዛሬም ያነጋግራል።
እናም ስለሚያሳስቡን ጉዳዮች ሰዓቱ ከረፈደ በኋላ ሳይሆን ዛሬ .. መነጋገር ለመነጋጋር ያህል ብቻም ሳይሆን ለመግባባት እና አንዳች ጠቃሚ መላ ለመሻት፤ መንገዱ ተጀምሯል።
በዛሬው የአገር ጉዳይ ሦሥት እንግዶች ከአዲስ አበባ ጋብዘናል።
“የሁላችንም በሆነች አገር ለሁላችንም የሚበጁ የሕይወት መላዎች” የሚሉ ይመስላል፤ የዛሬዎቹ “የአገር ጉዳይ” ባለተራዎች በወጋቸው።
የአዲስ አበባው የመጽሔት የወግ መስኮት ሲከፈት “ስለ ነፋስ” የተቀናበረ ዝግጅት በድምጹ መስኮት “ውልብ” ይላል። ከንባብ የፈጠነ ስለሚመስለው የድርሰት አጻጻፍ ፍጥነት ከአሥራ አምስት በላይ መጻሃፍት ደራሲ ጋር የተካሄደ ሌላ ወግ ተካቷል።
የፌስቡክ አስተያየት መስጫ