በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የአገር ጉዳይ:- ወደ የት እየሄድን ነው?


ተወያዮቹ:-አቶ ያሬድ ጥበቡ እና ፕሮፌሰር ዳንኤል ተፈራ
ተወያዮቹ:-አቶ ያሬድ ጥበቡ እና ፕሮፌሰር ዳንኤል ተፈራ

“ይሄንን ነገር በፖለቲካ መልክ ማየት አንችልም። ለዚህ ችግር መፍትሔ የሚያመጣው ችግሩን የፈጠረው ሕወአት ነው።” ፕሮፌሰር ዳንኤል ተፈራ። “ሕወአት በዚህ ላይ መፍትሔ ሊያመጣ አይችልም። ኢሕአዲግ ውስጥ ያለውም አመራር ቢሆን እየደከመ ከመሄዱ ጋር በተያያዘ፤ ያን የሚመጣጠን ሚና እንዲቀበል ነው ግፊት መደረግ ያለበት።” አቶ ያሬድ ጥበቡ።

ክፍል አንድ:- የት ነው ያለነው? .. የግለሰብ ነጻነት፥ ማንነትና ዜግነት?
please wait

No media source currently available

0:00 0:24:38 0:00
ክፍል ሁለት:- ሃገር ለገጠሟት ፈተናዎች መፍትሔው የፖለቲካ ወይስ የሌላ?
please wait

No media source currently available

0:00 0:13:23 0:00
ክፍል ሦሥት:- ለመሆኑ ወደ የት እየሄድን ነው?
please wait

No media source currently available

0:00 0:20:01 0:00

“የት ነው ያለነው? .. እረ ለመሆኑ ወደ የት እያመራን ይሆን?” በሚል ጥያቄ የሚንደረደረው የሳምንቱ የአገር ጉዳይ ውይይት እንደ ቀደሙት ሁሉ በዚያች አገር ነገ ሁነኛ መንገዶችና አቅጣጫዎች ዙሪያ ሊነጋገር ሁለት እንግዶች ጋብዟል።

አዎን! “የአገር ጉዳይ” ዛሬም ዘለቄታ ባላቸውና የሁላችንም በሚሆኑ ግቦች ዙሪያ ያተኩራል። የአንድ አገርና ሕዝብ ፈተናዎች፥ የመውጫ መንገዶችና ተሥፋ።

መንታ መንገድ ላይ ያለች በምትመስለው ሃገር ሰሞንኛ ይዞታዎች ዙሪያ የሚያጠነጥነው የሃሳብ ጉዞ ትላንትናና ዛሬያችንን ቃኘት ለማድረግ እናም ነገአችን የሚያጠላውን ደመና ለመግፈፍ የሚግዙ አወያይ ጭብጦችን ለመፈንጠቅ የታለመ ነው።

ከዓመት በፊት ገና ይህን ልዩ ፕሮግራም “ሀ” ብለን ስንጀምር ባስተዋወቅንበት መንፈስ በእነኚህ “ያሳስባሉ” እና “ያነጋግራሉ” በተባሉ “የአገር ጉዳይ” ሃሳቦች ዙሪያ እናንተ አድማጮቻችንም በያላችሁበት እርስ-በእርስ ትወያዩና “ይበጃል” የምትሉትንም ታደርሱን ዘንድ በአክብሮት ተጋብዛችኋል። ተወያዮች አቶ ያሬድ ጥበቡ እና ፕሮፌሰር ዳንኤል ተፈራ ናቸው።

የውይይቱን ቀዳሚ ክፍል እነሆ!

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG