በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ምንነት


ፎቶ ፋይል
ፎቶ ፋይል

የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ የጣላቸውን ገደቦችና አፈፃፀሙን የሚመለከቱ ማብራሪያዎች ከመንግሥት እየወጡ ሲሆን በተለያዩ መድረኮች ላይም ውይይቶች እየተካሄዱ መሆናቸው ታውቋል፡፡

የኮማንድ ፖስቱ ፅ/ቤት የሆነው የመከላከያ ሚኒስቴሩ የበላይ የሆኑት የመከላከያ ሚኒስትሩ አቶ ሲራጅ ፈጌሣ ክልከላ የተጣለባቸውንና እርምጃ ያስወስዳሉ ያሏቸውን እንቅስቃሴዎችና አካባቢዎች ለመንግሥቱ መገናኛ ብዙኃን ዘርዝረዋል፡፡

የኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግረስ ሊቀመንበርና የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ አንድነት ምክትል ሊቀ መንበር ዶ/ር መረራ ጉዲና የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ “የፖለቲካ ምኅዳሩን የበለጠ ለመዝጋት መንቀሳቅስ ነው” ብለውታል፡፡

ቬኦኤ ያነጋገራቸው የሕግ ባለሙያውና በአውስትራሊያ ሜሊበርን ዩኒቨርስቲ የሕግ ተመራማሪ የሆኑት ዶ/ር ፀጋዬ አራርሳ ከቪኦኤ ጋር ባደረጉት ቃለ-ምልልስ ሕገ-መንግሥቱ ስለአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ የሚናገረውን፣ በሕገ-መንግሥታዊና በአስቸኳይ ጊዜ ሁኔታ መካከል ስላለው ልዩነትና ግንኙነት አብራርተው

“የሰላማዊ ትግሉን መድረክ ያጠፋና ለማሰፈፀምም አስቸጋሪ የሆነ ሕጋዊ ሕገ-ወጥነት ነው” ብለውታል፡፡

ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያድምጡ።

የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ምንነት
please wait

No media source currently available

0:00 0:09:04 0:00

XS
SM
MD
LG