በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በጌዲኦ ዞን የ23 ሰው ሕይወት መጥፋቱን የክልሉ መንግሥት አረጋገጠ


ጌዲኦ ዞን
ጌዲኦ ዞን

በደቡብ ክልል በጌዲኦ ዞን በሦስት ወረዳዎች ባሉ የተለያዩ ከተሞች፤ በዲላ፣ በይርጋ ጨፌ፣በወናጎ፣ በፍስሃገነትና በወረዳዎቹ አካባቢ ባሉ ከተሞች “በተፈጠረ ግጭት ከአካባቢው ተወላጆች በተሰነዘረብን ድንገተኛ ጥቃት ቁጥራቸው ለጊዜው ያልታወቁ ሰዎች ተገደሉ፣ ንብረታችን ተቃጠለ አሁን ቤተክርስቲያ ከተጠለልን አራኛ ቀናችን ነው” ሲሉ ያነጋገርናቸው የአካብባቢው ነዋሪዎች ተናገሩ።

የክልሉ መንግስት ግጭቱ የተነሳው በነጋዴው ማኅበረሰብ እና በጌዲዮ ዞን ሕብረት ስራ ማኀበር መካከል በነበረ የመሬት ክርክር ምክንያት እንደሆነ ገልጾ በዚህም የ23 ሰዎች ሕይወት ጠፍቷል ብሏል። 25 ሺህ ደግሞ ተፈናቅሏል።

በክልል በጌዲኦ ዞን ፍስሃገነት ከተማ ነዋሪ የሆኑና ያነጋገርናቸው ነዋሪዎች እንደተናገሩት በዚህ አከባቢ በ1998 ዓ.ም ተመሳሳይ ግጭት ተነስቶ እንደነበር ይናገራሉ። ከዐስር ዓመት በኋላ በድጋሚ ድንገት በተነሳ ጥቃት ከፍተኛ አደጋ እንደረሰባቸ ይናገራሉ። ይህ አደጋ ከመድረሱ በፊት ግን ከጌዴኦ ተወላጆች ጋር እንደ ዕቁብ፣እድርና ቀብር የመሳሰሉትን ማኅበራዊ ሕይወቶች ሳይቀር በሰላም አብረው እንደሚያከናወኑ ገልጸው በድንገት በተከሰተው አደጋ መደናገጣቸውን ይናገራሉ።

ጽዮን ግርማ ዘገባ አላት።

ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምጽ ፋይል ያድምጡ።

በጌዲኦ ዞን የ23 ሰው ሕይወት መጥፋቱን የክልሉ መንግሥት አረጋገጠ
please wait

No media source currently available

0:00 0:06:55 0:00

በሌላ በኩል በባህርዳር ከተማ የቤት ውስጥ መቀመጥ አድማ መጠራቱን ነዋሪዎቹ ይናገራሉ።

XS
SM
MD
LG