ዋሽንግተን ዲሲ —
በኢትዮጵያ የአስቸኳይ ጊዜ ዐዋጁ ከታወጀ በኋላ የሞባይል ኢንተርኔት ሙሉ ለሙሉ መዘጋቱ እንዲሁም እንደ ፌስቡክ ያሉ ማኅበራቢ መገናኛዎች እንደ ቫይበር የመሳሰሉ የቴሌ ኮሙዩኒኬሽን መተግበሪያ አፕሊኬሽኖች አገልግሎት እንዳይሰጡ መታገዳቸው በዋነኛነት ብቸኛውን የመንግሥት ቴሌኮሙዩኒኬሽን ኩባንያ ኢቲዮ ቴሌኮምን እንደሚጎዳው ጥናቶች አመለከቱ።
ተገልጋዩን ደግሞ ማኅበራዊ ትስስሩን እንደሚጎዳው መረጃ የማግኘት መብቱን እንደሚያሳጣው በኦሪገን ዩኒቨርስቲ የሚዲያ ጥናት የዶክትሬት ተማሪው አቶ እንዳልካቸው ኃይለሚካኤል ለአሜሪካ ድምጽ ገልጿል።
ጽዮን ግርማ አቶ እንዳልካቸው ኃይለሚካኤልን አነጋግራ ተከታዩን ዘግባለች።
ዝርዝሩን ከተያያዘው ድምጽ ያዳምጡ።