በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ኢትዮ ቴሌኮም በግማሽ ዓመት 14 በመቶ የትርፍ ጭማሪ አስመዘገብኩ አለ


ኢትዮ ቴሌኮም፣ አዲስ አበባ
ኢትዮ ቴሌኮም፣ አዲስ አበባ

በመንግስት የሚተዳደረው ኢትዮ ቴሌኮም፣ በግማሽ ዓመት ውስጥ ትርፉ 14 በመቶ ማደጉን አስታውቋል። የሞባይል የገንዘብ አገልግሎት የሆነው ቴሌ ብር ለትርፉ አስተዋጽኦ ማድረጉ ተነግሯል።

ከወለድ ከታክስና ከሌሎችም ወጪዎች በፊት አጠቃላይ ትርፉ 19.77 ብሊዮን ብር መሆኑና፣ አጠቃላይ ገቢው ደግሞ በ26 በመቶ በማደግ 42.86 ቢሊዮን ብር መድረሱን የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ሥራ አስፈጻሚ ፍሬሕይወት ታምሩ ዛሬ አስታውቀዋል።

በግንቦት 2015 የተጀመረው የቴሌ ብር አገልግሎት ተጠቃሚዎች ቁጥር ወደ 41 ሚሊዮን ማደጉን የገለጹት ሥራ አስፈጻሚዋ፣ አጠቃላይ የቴሌፎን ደንበኞች 74.6 ሚሊዮን ደርሷል ብለዋል። በቴሌ ብር የተላለፈው ገንዘብም 910.7 ቢሊዮን ብር ነበር ብለዋል።

ኢትዮ ቴሌኮም፤ በጥቅምት 2015 ሥራውን ከጀመረው የመጀመሪያ የግል ኩባንያ ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ ጋር እንደሚፎካከር ያመለከተው የሮይተርስ ዘገባ፣ በአገሪቱ የሚታየው ተደጋጋሚ የፀጥታ ችግር፣ የሕግ መቀያየር እና መንግስት በጥብቅ የሚቆጣጠረውን ኢኮኖሚ ክፍት የማድረግ ቁርጠኝነቱ ጥያቄ ውስጥ በመውደቁ፣ ሌሎች የግል ኩባንያዎች ፊታቸውን እንዲያዞሩ አድርጓል ብሏል።

ኦሬንጅ የተሰኘው የፈረንሣይ የቴሌኮም ኩባንያ ከኢትዮ ቴሌኮም 45 በመቶ ድርሻ ለመግዛት የነበረውን ሂደት ባለፈው ህዳር አቋርጧል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG