በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ኢትዮጵያ ለተጨማሪ የግል ቴሌኮም አገልግሎት ጨረታ አወጣች


ኢትዮጵያ የቴሌኮሚኒኬሽን አገልግሎቷን ይበልጥ ለግል ዘርፉ ክፍት ለማድረግ ለሁለተኛ የግል ኩባንያ ፈቃድ ለመስጠት ጨረታ ማውጣቷን የኤኤፍፒ ዘገባ አመልክቷል።

“በዓለም ዝነኛ የሆኑ የቴሌኮም ኮባንያዎች ኢኮኖሚዋ በፍጥነት በማደግ ላይ በምትገኘው አገር ገብተው የዕድሉ ተጠቃሚ እንዲሁኑ ንጋብዛለን” ሲል የኢትዮጵያ ኮሚኒኬሽን ባለሥልጣን ትናንት ዓርብ ባወጣው ጨረታ ላይ አስታውቋል።

የኬንያው ሳፋሪኮም በኢትዮጵያ የቴሌኮም አገልግሎት በመስጠት የመጀመሪያው የግል ኩባንያ ሆኗል። የደቡብ አፍሪካው ኤም ቲ ኤን በጨረታው ያቀረበው ገንዘብ ዝቅተኛ በመሆኑ ውድቅ ተደርጓል። ባለፈው ጥቅምት ሥራውን የጀመረው ሳፋሪኮም እስከ አሁን 2.1 ሚሊዮን ደንበኞች ሲኖሩት፣ ወደ 10 ሚሊዮን የማሳደግ ዕቅድ እንዳለው አስታውቋል። ሳፋሪኮም በቅርቡ ገንዘብ የማስተላለፍ ፈቃድ ከብሄራዊ ባንክ አግኝቷል። ለውጪ ኩባንያ የተሰጠ የመጀመሪያው ፈቃድ መሆኑ ታውቋል።

መንግስት ባለፈው የካቲት የኢትዮጵያን 45 በመቶ የቴሌኮም ገበያ ወደ ግል ለማዛወር ፍላጎት እንዳለው አስታውቆ ነበር።

XS
SM
MD
LG