በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በቀይ ሽብር በበርካታ ወጣቶች ግድያ የተጠረጠሩት አቶ እሸቱ ዓለሙና በዘ - ሄግ ያስቻለው ፍርድ ቤት


“የያዛችሁት የተሳሳተ ሰው ነው። “የእኔ ድርሻ የፕሮፖጋንዳ ሥራ ብቻ ነበር።” አቶ እሸቱ ዓለሙ። “ወንድሜና ሌሎች በጊዜው ታስረው የነበሩት ወጣቶች እንዲገደሉ ትዕዛዝ የሰጡት አቶ እሸቱ ስለመሆናቸው በፊርማቸው ያዘዙበትን ጨምሮ ብዙ ማስረጃ ተገኝቷል።” አቶ አብረሃም ብዙነህ ከከሳሽ አቃቤ ሕግ ምሥክሮች አንዱ።

በቀይ ሽብር ዘመቻ ወቅት በበርካታ ሰዎች ግድያ “እጃቸው አለበት” በሚል የተጠረጠሩት የኔዘርላንድ ዜግነት ያላቸው ኢትዮጵያዊ ጉዳይ በዘ ሄግ እየታየ ነው።

ባለፈው ሰኞ ባስቻለው ችሎት ጉዳያቸው መታየት የጀመረው የስልሳ ሶት ዓመቱ የቀድሞ የደርግ አባል አቶ እሸቱ ዓለሙ “ፈጽመዋል” በተባለው ወንጀል በጊዜው ታስረው ከሞት የተረፉና እንዲሁም የቤተሰብ አባሎቻቸው የተገደሉባቸው በዩናይትድ ስቴትስ እና በሌሎች አካባቢዎች ነዋሪ የሆኑ ሰባት ኢትዮጵያውያን ዛሬ የምስክርነት ቃላቸውን ሰጥተዋል።

እንደ አውሮፓውያን የዘመን አቆጣጠር በ1970ዎቹ በጎጃም ክፍለ ሃገር በደብረ ማርቆስ ከተማ “ተፈጽሟል” በተባለውና 75 ወጣቶች የተገደሉበት ወንጀል ነው ተጠርጥረው ከፍርድ ቤቱ የቀረቡት።

የያዛችሁት “የተሳሳተ ሰው ነው” ሲሉ ለፍርድ ቤቱ የመለሱት ተጠርጣሪ አቶ እሸቱ ዓለሙ “የእኔ ድርሻ የፕሮፖጋንዳ ሥራ ብቻ ነበር” ቢሉም፤ “የዚያ ክፉ ጊዜ ዘግናኝ በደል ሰለባዎች ነን” ያሉት ወገኖች ግን የምሥክርነት ቃላቸውን ለመስጠት የኔዘርላንድ መንግስት መቀመጫና የበርካታ የዓለም አቀፍ ችሎቶች መናሃሪያ ወደ ሆነችው ዘ ሄግ ከተማ አቅንተዋል።

አቶ አብረሃም ብዙነህ ከዋሽንግተን ዲሲ ወጣ ብላ የምትገኘው የቨርጂኒያዋ የፎልስ ቸርች ከተማ ነዋሪ ናቸው። በተጠርጣሪው አቶ እሸቱ ትዕዛዝ ከተገደሉት ወጣቶች አንዱ ታላቅ ወንድማቸው መሆናቸውን ይናገራሉ።

ከአቶ አብረሃም ጋር የተደረገውን ሙሉ ቃለ ምልልስና ሙሉ ዘገባውን ከዚህ ያድምጡ።

በቀይ ሽብር ግድያ ተጠርጣሪው አቶ እሸቱ ዓለሙ የክስ ሂደት
please wait

No media source currently available

0:00 0:06:06 0:00

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG