በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የግብር ተመኑ ሮሮ፤ የምሥራቅ ጎጃሟ ስናን እና የሰሜን ወሎዋ ዋድላ ክራሞት

በቅርቡ በመንግሥት የተጣለውን ግብር ግምት ተከትሎ ሰሞኑን በተለያዩ በአማራ ክልል በሚገኙ ከተሞች በራቸውን በመዝጋት ተቃውሟቸውን ሲገልፁ ከሰነበቱት የንግድ ድርጅቶች አንዳንዶቹ አሁንም በቅዋሜው መቀጠላቸውን ነዋሪዎች ገለፁ።

በቅርቡ በመንግሥት የተጣለውን ግብር ግምት ተከትሎ ሰሞኑን በተለያዩ በአማራ ክልል በሚገኙ ከተሞች በራቸውን በመዝጋት ተቃውሟቸውን ሲገልፁ ከሰነበቱት የንግድ ድርጅቶች አንዳንዶቹ አሁንም በቅዋሜው መቀጠላቸውን ነዋሪዎች ገለፁ።

በራቸውን ከፍተው አገልግሎት መስጠት በጀመሩት ደግሞ የግብር ተመኑን ለመቋቋም ከፍተኛ የዋጋ ጭማሪ ማድረጋቸውን ለአሜሪካ ድምፅ አስተያየት የሰጡ የአካቢው ነዋሪዎች እየተናገሩ ነው።

ቀደም ብሎ ይፋ በተደረገው ድንጋጌ በተገለፀው መሠረት የተተመነብን ግብር ከመክፈል አቅማችን በላይ ነውና ይቀነስልን የሚል አቤቱታ ያሰሙ ነጋዴዎች በመጠየቃቸው ብቻ ይልቁንም ከፍ ያለ የቀረጥ ተመን የተጣለባቸው መሆኑንም በእማኝነት ይናገራሉ።

በምሥራቅ ጎጃሟ ስናን ወረዳ ዋና ከተማዋ ረቡዕ ገበያ ያሉ የንግድ ቤቶች ዛሬም በራቸውን አልከፈቱም።

የሰሜን ወሎዋን ዋድላ ወረዳ ውሎም የአሜሪካ ድምፅ ካነጋገራቸው አንዳንድ ነዋሪዎቿ እንሰማለን።

ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።

የግብር ተመኑ ሮሮ፤ የምሥራቅ ጎጃሟ ስናን እና የሰሜን ወሎዋ ዋድላ ክራሞት
please wait

No media source currently available

0:00 0:09:55 0:00

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG