በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የኦሮምያ የዛሬ ሰልፎች


ላለፉት ተከታታይ ሣምንታት በየሥፍራው ሰልፎች ሲካሂዱባት በሰነበተችው ኦሮምያ ዛሬም በመቱ፣ በጊምቢና በፍቼ “ብዙ ሰው ተገኝቶባዋል” የተባሉ ሰላማዊ ሰልፎች መካሄዳቸው ተገልጿል።

ላለፉት ተከታታይ ሣምንታት በየሥፍራው ሰልፎች ሲካሂዱባት በሰነበተችው ኦሮምያ ዛሬም በመቱ፣ በጊምቢና በፍቼ “ብዙ ሰው ተገኝቶባዋል” የተባሉ ሰላማዊ ሰልፎች መካሄዳቸው ተገልጿል።

ለሦስት ቀናት እየተካሄዱ ካሉት የመቱ ሰልፎች ትናንት በአንድ አጋጣሚ ሰልፈኛው ላይ አስለቃሽ ጋዝ ተወርውሮ እንደነበረ አንድ የከተማዪቱ ነዋሪ ለዝግጅት ክፍላችን ገልፀው የሰንደቅ ዓላማ ቀን አከባበርም በዛሬው ሰልፍ ምክንያት መስተጓጎሉን አመልክተዋል።

በጊምቢ ከተማም ሰሞኑን ሰልፎች እየተካሄዱ መሆናቸውን አንድ የከተማዪቱ ነዋሪ ለቪኦኤ ገልፀው የሰልፉን መንፈስ ለመረበሽና ሰዉ ላይ ጥቃት እንዲደርስ ለማስደረግ የሞከሩ ግለሰቦች እንደነበሩ ተናግረዋል።

በሰላሌም ፍቼ ላይ ቁጥሩ የበዛ ሰው ከአካባቢው የወጡ ተሣታፊዎች ሁሉ የተገኙበት ሰልፍ መደረጉን እንዲሁ አንድ የከተማዪቱ ነዋሪ ገልፀውልኛል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ በቦረና ዞን ሰሞኑን በአንድ በኩል በመከላከያ ኃይሎች፤ በሌላ ደግሞ በሶዳ ቀበሌና አካባቢዋ ነዋሪዎች መካከል ተፈጥሮ የነበረው ግጭትና ውጥረት መፍትሄ ሳያገኝ የመከላከያ ኃይሉ አባላት ሰዉ ላይ ከባድ ድብደባ አድርሰው ጭነውታል ከተባለ ስንቅና ትቅጥ ጋር መንገዳቸውን ወደ ሶማሌ ክልል መቀጠላቸው ተሰምቷል።

በአካባቢው ለተፈጠረውን ውጥረት መፍትኄ ለማፈላለግ ፌደራል መንግሥቱ ልኳቸዋል የተባሉ ሁለት ሚኒስትር ዴኤታዎች ባሉበት ነው ሰዉ ላይ ጥቃቱ የተፈፀመው ብለዋል አንድ እማኝ ለቪኦኤ በሰጡት ቃል።

ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።

የኦሮምያ የዛሬ ሰልፎች
please wait

No media source currently available

0:00 0:14:38 0:00

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG