ዋሺንግተን ዲ.ሲ. —
ይህ የአስቸኩዋይ ጊዜ አዋጅና የአፈጻጸም መመሪያው መሠረታዊ የሆኑና በህገ መንግስቱ የተደነገጉ ዲሞክራሲያዊ መብቶችን እስከስድስት ወር ለሚደርስ ጊዜ ያቋረጠ ነው።
በዚህ የአስቸኳይ ጊዜ ሁኔታ ውስጥ የገደብ እርምጃዎቹ የመጀመሪያ ተጋላጭ ከህዝቡ ጀርባ ተቃዋሚ የፖለቲካ እንቅስቃሴዎች ናቸው። ሰላማዊ የትግል ሥልት የሚከተሉትም ሆኑ በተፃራሪው የሚሄዱት።
እናም እነዚህ ፓርቲዎች ይህንን አዋጅና መመሪያውን እንዴት ይሆን የሚገመግሟቸው?
ተቃዋሚና የሰማያዊ ፓርቲ ሊቀ መንበር ይልቃል ጌትነት ፡ የመኢአድ ምክትል ፕሬዚዳንት ሙሉጌታ አበበ፤ የአረና ትግራይ የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አንዶም ገብረ ሥላሴ ዛሬ ለቪኦኤ አስተያየቶቻቸውን ሰጥተዋል፡፡
የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡