በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

አወዛጋቢው የዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖም የዓለም የጤና ድርጅት ዳይሬክተርነት ዕጩነት


የዓለም የጤና ድርጅት ለመምራት የታጩ
የዓለም የጤና ድርጅት ለመምራት የታጩ

የኢትዮጵያ የቀድሞ የውጭ ጉዳይና የጤና ጥበቃ ሚኒስትር ዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖም የዓለም የጤና ድርጅት ለመምራት ከታጩ ሦስት ተወዳዳሪዎች አንዱ ናቸው።

የኢትዮጵያ የቀድሞ የውጭ ጉዳይና የጤና ጥበቃ ሚኒስትር ዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖም የዓለም የጤና ድርጅት/WHO/ ለመምራት ከታጩ ሦስት ተወዳዳሪዎች አንዱ ናቸው። የዓለሙ ድርጅት አባል ሀገራት በሚቀጥለው ሳምንት ድምፅ እንደሚሰጡ ይጠበቃል። የዶ/ር ቴድሮስ አድሃምች ዕጩነት በኢትዮጵያዊያን ዘንድ መከፋፈልን ፈጥሯል።

በአንድ ወገን ዶ/ር ቴድሮስ በኢትዮጵያ የጤና ዘርፍ እንዲሁም የዓለም አቀፍ ድርጅቶችን በመምራትና በጋራ በመሥራት ዘርፈ ብዙ ለውጦችና መሻሻሎችን አስመዝግበዋል የሚሉ ሲደግፏቸው፤ በአንፃሩ ዶ/ር ቴድሮስ ያገለገሉት መንግሥት የዜጎቹን መብት የሚገፉ፣ ፍትሃዊ የጤና አገልግሎቶችን ለዜጎች ማዳረስ ያልቻለና፤ እንደ ኮሌራ ያሉ በሽታዎችን የተለየ ስም በመስጠት “አጣዳፊ ተቅማጥና ትውከት” በሚል መድሃኒት እንዳይደርስ አድርጓል፤ ለዓለም ጤናም አሉታዊ የመሸፋፈን ሥራ ተሰርቷል በሚል፤ አጥብቀው በመቃወም ላይ ናቸው።

ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።

አወዛጋቢው የዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖም የዓለም የጤና ድርጅት ዳይሬክተርነት ዕጩነት
please wait

No media source currently available

0:00 0:05:29 0:00

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG