በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የኬንያ ፍርድ ቤት በ137 ህገወጥ የኢትዮጵያ ፍልሰተኞች ላይ ብይን አስተላለፈ

የኬንያ ፖሊስ ባለፈዉ አርብ በቁጥጥር ሥር ያዋላቸዉ 137 ህገ ወጥ የኢትዮጵያዉያ ፍልሰተኞች ላይ ትላንት ከሰዓት ብይን ሰጠ። በፍርዱም እያንዳንዳቸዉ 300 የአሜርካን ዶላር ወይም የ 6ወር እሥራት ተላልፎባቸዋል።

የኬንያ ፖሊስ ባለፈዉ አርብ በቁጥጥር ሥር ያዋላቸዉ 137 ህገ ወጥ የኢትዮጵያዉያ ፍልሰተኞች ላይ ትላንት ከሰዓት ብይን ሰጠ። በፍርዱም እያንዳንዳቸዉ 300 የአሜርካን ዶላር ወይም የ 6ወር እሥራት ተላልፎባቸዋል።

የኬንያ ፖሊስ ፍልሰተኞቹን በህገ ወጥ መንገድ ወደ ኬንያ ያመጧቸዉን ሁለት ግለ ሰቦች ማለትም ‘ደጀኔ ቻፋ ና ቻኮ ጂሎ’ን ምርመራ እያካሄደባቸዉ ይገኛል።

በናይሮቢ ያለዉ የኢትዮጵያ ኢምባሲ “ፍልሰተኞቹ ስለ መያዛቸዉም ሆነ መታሰራቸዉ የደረኝ መረጃ የለም” ሲል መልስ ሰጥተዋል።

በሞያሌ ወደ ኬንያ ቅርብ ጊዜ በህገ ውጥ መንገድ ገብተዋል የተባሉት 137 ኢትዮጵያዉያን ባለፈዉ አርብ ነበር በናይሮቢ፥ ካዮሌ በሚባል ሰፈር በቁጥጥር ሥር የዋሉት። ሰዎቹ በኬንያ ፖሊስ ቁጥጥር ሥር ከቆዩ ቦኋላ ትላንት ፍርድ ቤት ቀርበዉ እያንዳንዳቸዉ 300 የአሜርካ ዶላር ወይም የ6ወር እሥራት ተፈርዶባቸዋል።

ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።

የኬንያ ፍርድ ቤት በ137 ህገወጥ የኢትዮጵያ ፍልሰተኞች ላይ ብይን አስተላለፈ
please wait

No media source currently available

0:00 0:03:36 0:00

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG