በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ዶሮ የወባ መከላከያ ልትሆን ነው!


chicken on sale
chicken on sale

የወባ ትንኝ በከፍተኛ ሁኔታ የሚራባበት ቦታ ይኖሩ ከሆነ ዶሮዎችን ከመኝታዎ አጠገብ አድርጎ መተኛቱ ያዋጣል የሚል ጥናት በቅርቡ ተሰምቷል። የዶሮ የተፈጥሮ ጠረን የወባ ትንኝን አርቆ የሚያበር ሆኗል። ይህ ጠረን በወባ ምክንያት የሚከሰተውን ህመምም ለመከላከል ታላቅ አስተዋፆ እንዳለው በጥናቱ ተደርሶበታል።

የወባ ትንኝ ደምን በመምጠጥ በሽታዎችን ከአንዱ ወደ አንዱ በማስተላለፍ ይታወቃሉ። ከቤት እንስሳት ከብቶችን ጨምሮ የፍየሎች እና የበጎችን ደም ይመጣሉ፤ ዶሮን ግን የወባ ትንኝ አይነካም፤ በተፈጥሮ ጠረኗ ምክንያት።

በቅርቡ የሲውዲንና የኢትዮጵያ የጤና ተመራማሪዎች ከአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ጋር በመሆን የወባ ትንኝ ላይ ጥናትን አድርገው ነበር። በኢትዮጵያ በከፍተኛ የመራባት ቁጥሩ የሚታወቀውን አናፌለስ አራቤነሲስ /Anopheles arabiensis/ የተባለውን የወባ ትንኝ በመከላከል ዙሪያ በምስራቅ ወለጋ አስራ አንድ የመኖሪያ ቤቶችን መሰረት በማድረግ ነበር ጥናቱ የተጀመረው።ጥናቱ የወባ ትንኝ በብዛት የሚገኝበት ቦታ ነዋሪዎችን በፈቃደኝነት ያሳተፈም ነበር።

ለጥናቱ አናፌለስ አራቤነሲስ የወባ ትንኞች በመረብ ሰብስቦ በመያዝና በመኖሪያ ቤትና በከብት ማደሪያ ውስጥ በማስቀመጥ ትንኞቹ ከብትን ይሁን ሰውን በበለጠ እንደሚያጠቁ ለማወቅ ጥናት አድርገዋል። ተመራማሪዎቹ ከዶሮ በስተቀር ሁሉም በወባ ትንኞቹ መነከሳቸውን አረጋግጠዋል።

የአሜሪካ ድምፅ ሬድዮ የሳይንስ ፕሮግራም አጠናቃሪ ጀሲካ በርማን የዘገበችውን መስታወት አራጋው ታቀርበዋለች። ከበታች ያለውን የድምፅ ምልከት በመጫን ሙሉ ዘገባውን ያድምጡ።

ዶሮ የወባ መከላከያ ልትሆን ነው!
please wait

No media source currently available

0:00 0:02:28 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ

XS
SM
MD
LG