በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በሦስት የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ላይ ተጥሎ የነበረው እገዳ ተነሳ


ፎቶ ፋይል፦ አዲስ አበባ
ፎቶ ፋይል፦ አዲስ አበባ

ከተሰጣቸው ፈቃድ ውጪ ተንቀሳቅሰዋል በሚል ታግደው የነበሩ፣ በሰብአዊ መብት ጥበቃ ዙሪያ የሚሠሩ ድርጅቶች ዛሬ እግዳቸው ተነስቷል።

በኢትዮጵያ ሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ባለሥልጣን በኅዳር ወር ውስጥ በቀናት ልዩነት እግድ ተጥሎባቸው የነበሩት፣ የመብቶችና ዴሞክራሲ ዕድገት ማዕከል (ካርድ)፣ የሕግ ባለሙያዎች ለሰብአዊ መብቶች እና ስብስብ ለሰብአዊ መብቶች በኢትዮጵያ የተባሉ ድርጅቶች ናቸው፡፡

በሦስት የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ላይ ተጥሎ የነበረው እገዳ ተነሳ
please wait

No media source currently available

0:00 0:02:49 0:00

ለእግዱ ምክንያት ተብሎ የተጠቀሰው ደግሞ፣ ከተሰጣቸው ፈቃድ ውጪ ተንቀሳቅሰዋል፣ እንዲሁም የአገርንና የሕዝብን ጥቅም የሚጎዳ ተግባር አከናውነዋል የሚል ነበር፡፡

የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ባለሥልጣን ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ፋሲካው ሞላ፣ እግድ በተጣለባቸው የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ላይ “በአጭር ጊዜ ውስጥ የመጨረሻ ውሳኔ” እንደሚሰጥ ኅዳር 19 መግለጫ በሰጡበት ወቅት ገልጸው የነበረ ሲሆን፣ ዛሬ ታኅሣሥ 2 እግዱ መነሳቱ ታውቋል፡፡

ታግደው ከነበሩት ድርጅቶች አንዱ የኾነው የሕግ ባለሙያዎች ለሰብአዊ መብቶች ዋና ዳይሬክተር አቶ አምሃ መኮንን፣ እግዱ መነሳቱን የሚገልጽ ደብዳቤ ከማስጠንቀቂያ ጋራ እንደተሰጣቸው ተናግረዋል።

ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG