ኢትዮጵያ ውስጥ በቅርቡ ከታገዱት ሦስት የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች የሁለቱ አመራሮች የድርጅታቸው ሕልውና አደጋ ላይ መውደቁን ተናገሩ።
የመብቶችና ዴሞክራሲ ዕድገት ማዕከል (ካርድ) እና የሕግ ባለሞያዎች ለሰብአዊ መብቶች የተባሉ ሁለቱ የሲቪል ማኅበራት ድርጅት መሪዎች የባንክ ሂሳባቸው በመታገዱ ምክኒያት፣ ለሠራተኞች ደሞዝ መክፈልን ጨምሮ ምንም ዐይነት እንቅስቃሴ ማድረግ ባለመቻላቸው ችግር ውስጥ መውደቃቸውን ገለጹ።
ከኢትዮጵያ በሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ባለሥልጣን ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት ያደረገው ጥረት አልተሳካም። ይኹንና ኅዳር 19 ቀን 2017 ዓ.ም. የተቋሙ ምክትል ዲሬክተር አቶ ፋሲካው ሞላ፣ እየተከናወነ ነው ያሏቸው የማጣራት ሥራ ሲጠናቀቅ ውጤቱ እንደሚገለጽ በቅርቡ መናገራቸው ይታወሳል።
ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።
መድረክ / ፎረም