አዲስ አበባ፤ መቀሌ —
የትግራይ ብሄራዊ ክልላዊ መንግሥት፣ የሥራ አስፈፃሚ አካላትና የምርጫ ኮሚሽን ምርጫን በሚመለከት ያወጣው የምርጫ አዋጅ፣ ያሳለፏቸው ውሣኔዎችና የፈፀሟቸው ተግባራት “ከህገመንግሥቱ ጋር የሚቃረኑ” መሆናቸውን የፌዴሬሽን ምክር ቤት ዛሬ ባካሄደው አስቸኳይ ጉባዔ በየነ።
በዚህም መሠረት “በህገመንግሥቱ አንቀፅ 9 ንዑስ አንቀፅ 1 መሠረት እንዳልተደረጉ የሚቆጠሩ፣ የማይፀኑና ተፈፃሚነት የሌላቸው ናቸው” ሲል በሙሉ ድምፅ መወሰኑ ተገልጿል።
በዚሁ በዛሬው የፌዴሬሽን ምክር ቤት ውሣኔዎች ላይ የትግራይ ክልላዊ መንግሥት ቃል አቀባይ ወ/ሮ ሊያ ካሣ ለቪኦኤ በሰጡት ቃል ውሣኔው “ምክር ቤቱ በትግራይ ህዝብ ላይ ያለውን የመረረ ጥላቻ ያሳየ ነው” ብለዋል።
ከአዲስ አበባና ከመቀሌ የተጠናቀሩትን ዘገባዎች ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።