ዋሽንግተን ዲሲ —
በዚህ ቦታ በአደጋ ቤተሰቦቻቸውና በሕጋዊ መንገድ የሠሩትን ቤታቸውን ያጡ ሕጋዊ የቤት ካርታ የነበራቸው ፣ ተከራይተው ይኖሩ ከነበሩ መካከል የተወሰኑትን አነጋግረናል።
ጽዮን ግርማ ናት ዘገባውን ያሰናዳችው።
ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያድምጡ።
በአዲስ አበባ ከተማ "ቆሼ" ተበሎ በሚጠራው ቦታ ከደረሰው የመደርመስ አደጋ የተረፉ ቤተሰቦች አንዳንዶቹ ተገቢው እርዳታ አልተደረገልንም “ወሬውን እንጂ በተግባር ያየነው ነገር የለም” ሲሉ አማረሩ። የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳድር በ24 ሚሊዮን ብር ወጪ የተሰሩ 110 የመኖሪያ ቤቶች ለተጎጂዎች ማስረከቡን እና ሁሉንም በአንድ ማዕቀፍ አካቶ እንደሚያቋቁም በሀገር ውስጥ መገናኛ ብዙሃን ይፋ አድርጓል።
በዚህ ቦታ በአደጋ ቤተሰቦቻቸውና በሕጋዊ መንገድ የሠሩትን ቤታቸውን ያጡ ሕጋዊ የቤት ካርታ የነበራቸው ፣ ተከራይተው ይኖሩ ከነበሩ መካከል የተወሰኑትን አነጋግረናል።
ጽዮን ግርማ ናት ዘገባውን ያሰናዳችው።
ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያድምጡ።
የፌስቡክ አስተያየት መስጫ