No media source currently available
በአዲስ አበባ ከተማ "ቆሼ" ተበሎ በሚጠራው ቦታ ከደረሰው የመደርመስ አደጋ የተረፉ ቤተሰቦች አንዳንዶቹ ተገቢው እርዳታ አልተደረገልንም “ወሬውን እንጂ በተግባር ያየነው ነገር የለም” ሲሉ አማረሩ። የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳድር በ24 ሚሊዮን ብር ወጪ የተሰሩ 110 የመኖሪያ ቤቶች ለተጎጂዎች ማስረከቡን እና ሁሉንም በአንድ ማዕቀፍ አካቶ እንደሚያቋቁም በሀገር ውስጥ መገናኛ ብዙሃን ይፋ አድርጓል።