የመከላከያ ሚኒስትሩ አቶ ሲራጅ ፈጌሳ ትላንት ለአገር ውስጥ ጋዜጠኞች በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ "ከኤርትራ ከአርባ እስከ ሃምሣ የሚጠጉ ወታደሮች በየቀኑ ወደ ኢትዮጵያ ይገባሉ፤ በዛው ልክ ሲቪሎችም ይገባሉ፤ ምናልባት የአሁኑን ለየት የሚያደርገው በሰማይ መምጣቱ ብቻ ነው" ብለዋል፡፡
የኤርትራን መንግሥት አስተያየት ለማግኘት ያደረግነው ጥረት አልተሳካም።
ይሁንና የኢንፎርሜሽን ሚኒስትሩ አቶ የማነ ገብረመስቀል ለእንግሊዝ የዜና አውታር - ቢቢሲ በሰጡት መግለጫ ዜናውን "ውዳቂ" ሲሉ አጣጥለውታል፡፡
ለዝርዝሩ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡