በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የኤርትራ የጦር ጀትና አብራሪዎች እርሷ ዘንድ እንደሚገኙ ኢትዮጵያ አስታወቀች


ፎቶ ፋይል
ፎቶ ፋይል

የኤርትራ አየር ሐይል ንብረት የሆነች ሚግ 29 ተዋጊ አውሮፕላን ሁለት ፓይለቶችን ይዛ ወደ ኢትዮጵያ መግባትዋ የኢትዮጵያ ደህንነትና ጸጥታ ምንጮች ገለጹ፤ የኤርትራ ባለስልጣናት ዜናውን “ፍሬ ቢስ” ሲሉ ማጣጣላቸው ተዘግቧል።

ምንጮቹ ለቪኦኤ እንደገለጹት ‘ከራዳር እይታ ውጭ የመብረር አቅም ያላት የኤርትራ አየር ሐይል አውሮፕላን፣ ትላንት ጠዋት ከአስመራ ወደ ምዕራብ ኤርትራ አቅጣጫ በመብረር፣ የሰሜናዊ ምዕራብ የኢትዮጵያ ድንበር በማቋረጥ ወደ ሑመራ አከባቢ እንደደረሰችና በኢትዮጵያ አየር ሃይል ሚግ አውሮፕላኖች ታጅባ መቀሌ ወደ ሚገኘው የአየር ሃይል ካምፕ እንድታርፍ መደረጉን ስማቸውን ያልጠቀሱ የደህንነት ባለስልጣናት ለአሜሪካ ድምጽ ተናግረዋል።

የኤርትራ ባለስልጣናት ኢትዮጵያ ገባች ስለተባለችው ተዋጊ አውሮፕላን የሰጠው ዝርዝር ማብራሪያ ባይኖርም የማስታወቂያ ሚኒስትሩ አቶ የማነ ገብረመስቀል ለብርታንያ የዜና ምንጭ “ፍሬ ቢስ” ሲሉ ማጣጣላቸው ተዘግቧል።

የኢትዮጵያ የደህንነት ባለስልጣናት ክንፍ ቁጥሯ ZLIN 143 ኣውሮፕላን

አብራሪ መቶ አለቃ መብራህቱ ተስፋማርያምና አብሯቸው የነበረው ፓይለት አፈወርቅ ጸሐዬ ባልታወቀ ስፍራ “በመልካም” ሁኔታ ላይ እንደሚገኙ እነዚሁ ምንጮች ለቪኦኤ ገልጿል።

የኤርትራ መንግስት በጉዳዩ ላይ አስተያየት እንዲሰጥበት ያደረግነው ጥረት ይህ ዜና እስከተጠናቀረበት ሰዓት ማግኘት አልተቻለም፤ እንዳገኘን እናቀርባለን።

ሔኖክ ሰማእግዜር ዝርዝሩን ይዟል።

ዝርዝሩን ከተያያዘው ድምፅ ያዳምጡ፡፡

የኤርትራ የጦር ጀትና አብራሪዎች እርሷ ዘንድ እንደሚገኙ ኢትዮጵያ አስታወቀች
please wait

No media source currently available

0:00 0:01:39 0:00

XS
SM
MD
LG