ሰሞንኛው ወግ ቀጥሏል።
ያለፈው ሳምንት የኤርትራው ፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ የኢትዮጵያ ጉብኝትና ደማቅ አቀባበል፤ መሰንበቻውን አሥመራ ላይ የታየው ታላቅ የደስታ ስሜት እና ከዚያ ቀደም ብሎ በተከታታይ እውን የሆኑት ያልተጠበቁ ሁኔታዎች፤ አጠቃላይ ድባቡ በሁለቱ ጎረቤት አገሮች ኢትዮጵያና ኤርትራ ጉዳይ አዲስ ምዕራፍ ከፋች ተደርጎ ተወስዷል።
የተፈጠረውን ሁኔታ ምንነት እና የቀጣዩን ሂደት አቅጣጫዎች ጨምሮ በርከት ባሉ ጭብጥች ዙሪያ የታሪክ ምልከታ ለመፈንጠቅ የታለመ ተከታታይ ውይይት ነው።
ተወያዮች፡- በኢትዮጵያ እና ኤርትራ ጉዳዮች ላይ ሠፊ ጥናት ያካሄዱ የታሪክ ምሁራን ናቸው።
ፕሮፌሰር ገብሩ ታረቀኝ ቀደም ሲል በዩናይትድ ስቴትሱ የኒውዮርክ ስቴት ዩኒቨርሲቲ ለረዥም ዓመታት በታሪክ መምሕርነት ያገለገሉ የታሪክ ምሁርና የግጭቶች ጥናት ባለ ሞያ ናቸው። በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲም በተለያዩ ኃላፊነቶችና በመምሕርነት አገልግለዋል።
ፕሮፌሰር ተከስተ ነጋሽ የስዊዲኑ የUppsala ዩኒቨርሲቲ ለረዥም ዓመታት በታሪክ መምሕርነትና እንዲሁም በጥናት እና ምርምር አገልግለዋል።
ፕሮፌሰር ሹመት ሲሻኝ በዩናይትድ ስቴትሱ የክርስቶፈር ኒውፖርት ዩኒቨርሲቲ ለረዥም ዓመታት በታሪክ መምሕርነት ያገለገሉና ባሁኑ ወቅት በዩናይትድ ስቴትስ ዓለም አቀፍ የትምሕርት ፕሮግራም አማካኝነት በባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ በምርምር እና በማስተማር አገልግሎት ላይ ያሉ ናቸው።
ተከታታይ ውይይቶቹን ከዚህ ያድምጡ።
የቀደሙትን ውይይቶች ለመከታተል ከዚህ በታች የሚያገኙትን አያያዥ ጽሁፍ ይጫኑ፡-https://amharic.voanews.com/a/ethiopia-eritrea-relationship-historical-perspectives-with-professors-shumet-sishagne-and-professor-gebru-tarekegne-voa-alula-kebede-july-20/4482071.html
የፌስቡክ አስተያየት መስጫ