በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ኢትዮጵያና ኤርትራ .. የሁለት ጎረቤታሞች ታሪክ


መሰንበቻውን አሥመራ ላይ የታየው ታላቅ የደስታ ስሜት እና ከዚያ ቀደም ብሎ በኢትዮጵያ የሆነው በሁለቱ ጎረቤት አገሮች ኢትዮጵያና ኤርትራ ጉዳይ አዲስ ምዕራፍ ከፋች ተደርጎ ተወስዷል።

የተፈጠረውን ሁኔታ ምንነት እና የቀጣዩን ሂደት አቅጣጫዎች ጨምሮ በርከት ባሉ ጭብጥች ዙሪያ የታሪክ ምልከታ ለመፈንጠቅ የታለመ ተከታታይ ውይይት ነው።

ተወያዮች፡- በኢትዮጵያ እና ኤርትራ ጉዳዮች ላይ ሠፊ ጥናት ያካሄዱ የታሪክ ምሁራን ናቸው።
ፕሮፌሰር ገብሩ ታረቀኝ ቀደም ሲል በዩናይትድ ስቴትሱ የኒውዮርክ ስቴት ዩኒቨርሲቲ ለረዥም ዓመታት በታሪክ መምሕርነት ያገለገሉ የታሪክ ምሁርና የግጭቶች ጥናት ባለ ሞያ ናቸው። በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲም በተለያዩ ኃላፊነቶችና በመምሕርነት አገልግለዋል።

ፕሮፌሰር ሹመት ሲሻኝ በተመሳሳይ በዩናይትድ ስቴትሱ የክርስቶፈር ኒውፖርት ዩኒቨርሲቲ ለረዥም ዓመታት በታሪክ መምሕርነት ያገለገሉና ባሁኑ ወቅት በዩናይትድ ስቴትስ ዓለም አቀፍ የትምሕርት ፕሮግራም አማካኝነት በባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ በምርምር እና በማስተማር አገልግሎት ላይ ያሉ ናቸው። ተከታታይ ውይይቱን ከዚህ ያድምጡ።

ኢትዮጵያና ኤርትራ .. የሁለት ጎረቤታሞች ታሪክ .. ክፍል አንድ
please wait

No media source currently available

0:00 0:09:21 0:00
ኢትዮጵያና ኤርትራ .. የሁለት ጎረቤታሞች ታሪክ .. ክፍል ሁለት
please wait

No media source currently available

0:00 0:14:40 0:00

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG