ዋሽንግተን ዲሲ —
በኢትዮጵያና በኤርትራ መካከል የነበረውን የውጥረት ጦርነት በይፋ ለማስቆም ስምምነት መፈረሙን ሁለቱ ሀገራት አስታወቀዋልአስታወቁ። የጠቅላይ ሚኒስትሩ ጽ/ቤት ልዩ ኃላፊ አቶ ፍጹም አረጋ፤ ሁለቱ ሀገራት በፖለቲካዊ፣ ኤኮኖሚያዊ፣ ማኅበራዊ፣ በፀጥታና በደህንነት ጉዳዮች በጋራ ለመስራት የሚያስችሉ ጉዳዮችን ያካተ ስምምነት መፈረሙን ለአሜሪካ ድምፅ አብራርተዋል።
በሌላ በኩል የኤርትራው ማስታወቅያ ሚኒስትር የማነ ገብረመስቀል የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትርና የኤርትራ ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ አስመራ ከተማ ውስጥ ስምምነቱን ሲፈርሙ የሚያሳዩ ምስሎች በትዊተር ገፃቸው ላይ አስፍረዋል።
በሁለቱም ሀገሮች መካከል የነበረው “ጦርነት አብቅቶ አዲስ የሰላምና የወዳጅነት ዘመን ተጀምሯል ሲሉም ጽፈዋል።
ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያድምጡ።
የፌስቡክ አስተያየት መስጫ