በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ኢትዮጵያ፣ ኤርትራ እና ደቡብ ሱዳን የጋራ የትብብር ፕሮጀክቶች


የኤርትራ ፕሬዚዳንት ኢሣያስ አፈወርቂ፣ የደቡብ ሱዳን ፕሬዚዳንት ሳልቫኪር ማያርዲት እና የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐብይ አህመድ
የኤርትራ ፕሬዚዳንት ኢሣያስ አፈወርቂ፣ የደቡብ ሱዳን ፕሬዚዳንት ሳልቫኪር ማያርዲት እና የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐብይ አህመድ

ኢትዮጵያ፣ ኤርትራ እና ደቡብ ሱዳን የጋራ የትብብር ፕሮጀክቶችን ለመተግበር ስምምነት ላይ መድረሳቸው ተዘገበ። ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐብይ አህመድ፣ ፕሬዚዳንት ኢሣያስ አፈወርቂ እና ፕሬዚዳንት ሳልቫኪር ማያርዲት ትናንት የሦስትዮሽ ውይይቱን ያደረጉት በደቡብ ሱዳን ጁባ ከተማ መሆኑን የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል።

ስምምነት የተደረሰባቸው የትብብር ፕሮጀክቶች፣ የቀጠናውን የኢኮኖሚ ትስስር በማፋጠን ለጋራ ተጠቃሚነት እንደሚረዱ ታምኖባቸዋል። ሃገራቱ በቀጠናዊና ዓለምቀፋዊ ጉዳዮች ላይ በትብብር መስራት የሚችሉበትን አግባብ ማመቻቸት በሚቻልበት ጉዳይ ላይም በስፋት መክረዋል ተብሏል።

በተጨማሪም በውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮቻቸው በኩል የሃገራቱን ኢኮኖሚያዊ ውኀደት ለማምጣት እንደሚሠሩ ተስማምተዋል። ከደቡብ ሱዳን ወቅታዊ ሁኔታ ጋር በተያያዘም - በደቡብ ሱዳን ዘላቂ ሰላምን ለማምጣት በጋራ መስራት እንደሚገባ አጽንዖት ሰጥተዋል።

ኢትዮጵያ፣ ኤርትራ እና ደቡብ ሱዳን የጋራ የትብብር ፕሮጀክቶች
please wait

No media source currently available

0:00 0:01:53 0:00

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG