በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ከትምህርት የራቁ ተማሪዎች ለተለያዩ ጥቃቶች እየተጋለጡ ናቸው - ባለሞያዎች


ከትምህርት የራቁ ተማሪዎች ለተለያዩ ጥቃቶች እየተጋለጡ ናቸው - ባለሞያዎች
please wait

No media source currently available

0:00 0:05:23 0:00

ከትምህርት የራቁ ተማሪዎች ለተለያዩ ጥቃቶች እየተጋለጡ ናቸው - ባለሞያዎች

በኢትዮጵያ፣ በሰው ሠራሽ እና ተፈጥሯዊ ችግሮች ምክንያት ከትምህርት የራቁ ልጆች፣ በትምህርት ቤቶች የሚያገኙትን ጥበቃ እና ከለላ ስለሚያጡ፣ ለተለያዩ ጥቃቶች እንደሚዳረጉ ባለሞያዎች ገለጹ፡፡

በዘንድሮው የትምህርት ዘመን፣ በሀገር አቀፍ ደረጃ አምስት ሚሊዮን ተማሪዎች ከትምህርት ገበታ ውጭ እንደኾኑ መንግሥት አስታውቋል፤ ባለሞያዎቹ ደግሞ፣ ኹኔታው በአገሪቱ ማኅበረ ኢኮኖሚያዊ ቀውስ እንደሚያስከትል ለአሜሪካ ድምፅ ተናግረዋል፡፡

በጉዳዩ ላይ አስተያየት የሰጠው የኢትዮጵያ መምህራን ማኅበር፣ በልዩ ልዩ የአገሪቱ ክፍሎች በግጭት እና በድርቅ ምክንያት በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ተማሪዎች ከትምህርት እንደራቁ ገልጾ፣ በጦርነት ወቅት ለትምህርት ቤቶች ጥበቃ እየተደረገ እንዳልኾነ አመልክቷል፡፡

ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG