በአማራ ክልል፣ ባለፈው ዓመት መጨረሻ በተቀሰቀሰውና ተለዋዋጭ ገጽታ እያሳየ በተስፋፋው ግጭት፣ በትምህርት ዘመኑ የመጀመሪያ መንፈቅ 3ሺሕ700 የሚደርሱ ትምህርት ቤቶች እስከ አሁን ተዘግተው እንደሚገኙ፣ የክልሉ ትምህርት ቢሮ አስታወቀ፡፡
የክልሉ ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ሙሉነሽ ደሴ፣ ከአሜሪካ ድምፅ ጋራ በነበራቸው ቆይታ፣ በጸጥታ ችግር ምክንያት በትምህርት ዘመኑ ከ2ነጥብ6 በላይ የክልሉ የአንደኛ እና ሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎች፣ ከትምህርት ገበታ ውጭ መሆናቸውን ገልጸዋል፡፡
በተለይ፣ ከገጠር ቀበሌዎች በአቅራቢያ ወደሚገኙ ከተሞች ልጆቻቸውን ልከው የሚያስተምሩ ወላጆች፣ የጸጥታ ችግር ስጋት እንደሆነባቸው ኃላፊዋ አመልክተዋል፡፡
ግጭት በተካሔደባቸው የክልሉ አካባቢዎች፣ ተማሪዎችን ወደ ትምህርት ለመመለስ በሚከናወነው ጥረት ላይ ከባለድርሻ አካላት ጋራ በአዲስ አበባ ምክክር እየተደረገ ነው፡፡
ያነጋገርናቸው የተማሪ ወላጆች እና ተማሪዎችም ትምህርት በቅርቡ ካልተጀመረ በክልሉ ማኅበራዊ ቀውስ ይፈጠራል የሚል ስጋት እንዳላቸው ተናግረዋል።
ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።
መድረክ / ፎረም