በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በራያ ቆቦ የምግብ እጥረት


ራያ ቆቦ
ራያ ቆቦ

በሰሜን ወሎ ዞን በራያ ቆቦ እና በሃብሩ ወረዳዎች 54 የገጠር ጣብያዎች ባለፈው ክረምት ያገኙት ዝናብ አነስተኛ በመሆኑ፣ ይህ ነው የሚባል ምርት እንዳላገኙ ገበሬዎች ገለጹ።

በሰሜን ወሎ ዞን በራያ ቆቦ እና በሃብሩ ወረዳዎች 54 የገጠር ጣብያዎች ባለፈው ክረምት ያገኙት ዝናብ አነስተኛ በመሆኑ፣ ይህ ነው የሚባል ምርት እንዳላገኙ ገበሬዎች ገለጹ።

በራያ ቆቦ ወረዳ ቀዩ ጋራ በተባለው ኣከባቢ የሚኖሩ ወይዘሮ ሽሽት ሞላ እንደሚሉት በተለይ በኣሁኑ ሰዓት እየጣለ ያለው ዝናብ ከክረምቱ ድርቅ ያላጠቃውን የማሽላ እና የጤፍ ክምር ያበላሽብናል የሚል ስጋት አሰምተዋል።

ሌላው የኣከባቢው ነዋሪ ኣርሶ ኣደር ምስጋና ሰማው በኣሁኑ ሰዓት በማሳ ላይ የቀረው ሰብል በዝናብ እጥረት ምክንያት ምንም እንዳላፈራና ለከብቶች መኖ እንዲሆን እየሰበሰቡት እንደሚገኙ ገልፀው ከዚሁ ድርቅ የተነሳ ህዝቡ በጣም እንደተራበ ይናገራሉ።

ገበሬዎቹ መንግስት የእህል እርዳታ መስጠቱን የገለፁ ቢሆንም በቂ እንዳልሆነ በኣፅንኦት ተናግረዋል። ይህም ሆኖ በኣከባቢው ከኣሁን በፊት በረሃብ ምክንያት የሞተ መኖሩን እንደማያውቁ ኣርሶ ኣደሮቹ ለአሜሪካ ድምፅ ዘጋቢ ገልጸዋል።

በሰሜን ወሎ ዞን አደጋ መከላከልና ምግብ ዋስትና ፕሮግራም ማስተባበርያ ጽህፈት ቤት ተጠሪ አቶ መሐመድ ያሲን በዞኑ ውስጥ በአጋጠመው የዝናብ እጥረት የተራበ ሰው አለመኖሩን ገልጸዋል። ዝርዝሩን ግርማይ ገብሩ አጠናቅሮ ልኮታል ከተያያዘው የድምጽ ፋይል ያዳምጡ።

በራያ ቆቦ የምግብ እጥረት
please wait

No media source currently available

0:00 0:10:16 0:00

XS
SM
MD
LG