በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ለጋሽ ሀገሮች ለኢትዮጵያ የእርዳታ ጥሪ መልስ እንዲሰጡ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ ጠየቁ


 የተመድ ዋና ፀኃፊ አንቶንዮ ጉቴሬዝ
የተመድ ዋና ፀኃፊ አንቶንዮ ጉቴሬዝ

ኢትዮጵያ የተከሰተውን ድርቅ ለመቋቋም ላቀረበቸው ጥሪ ዓለም አቀፍ ማኅበረሰብ አፋጣኝ ምላሽ እንዲሰጥ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዋና ፀኃፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ ጠየቁ፡፡

ኢትዮጵያ የተከሰተውን ድርቅ ለመቋቋም ላቀረበቸው ጥሪ ዓለም አቀፍ ማኅበረሰብ አፋጣኝ ምላሽ እንዲሰጥ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዋና ፀኃፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

ዋና ፀኃፊው ጥሪውን ያቀረቡት በዚሁ ድርቅ ላይ ከተወያዩና ከትናንት በስቲያ ማታ በተጠናቀቀው ስብሰባ ላይ ነው፡፡

በተባበሩት መንግሥታት የስብሰባ ማዕከል በትናንትናው ዕለት የተካሄደው ስብሰባ የኢትዮጵያ መንግሥት በተለይ በአርብቶ አደር አካባቢዎች አዲስ ድርቅ መከሰቱን ይፋ ካደረገ በኋላ የተካሄደ የመጀመሪያው ከፍተኛ እና ዓለም አቀፍ ስብሰባ ነው፡፡ በዚሁ ድርቅ ምክንያት 5.6 ሚሊዮን ኢትዮጵያውያን የአስቸኳይ ጊዜ የምግብ እርዳታ ያስፈልጋቸዋል፡፡

የእነርሱን ፍላጎት ለሟሟላት እና ለተያያዥ መላሾች የሚጠበቀው የገንዘብ መጠን ደግሞ ዘጠን መቶ አርባ ስምንት ሚሊዮን ዶላር መሆኑ ተልጿል፡፡

ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።

ለጋሽ ሀገሮች ለኢትዮጵያ የእርዳታ ጥሪ መልስ እንዲሰጡ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ ጠየቁ
please wait

No media source currently available

0:00 0:04:58 0:00

XS
SM
MD
LG