በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

“ከ2ሽህ በላይ ሰዎች ተፈትተዋል” አቶ ሲራጅ ፈጌሳ


ፎቶ ፋይል
ፎቶ ፋይል

ኢትዮጵያ ውስጥ በቅርቡ በተካሄዱ ተቃውሞዎች ምክንያት ታሰረው የነበሩ ወደ 2ሽህ ያህል ሰዎች “ትምህርትና ምክር” ከተሰጣቸው በኋላ ተለቀዋል መንግሥታዊው ፋና ዜና አውታር እንደዘገበው።

በራድዮ ፋና ዘገባ መሠረት በተቃውሞው ወቅት ለታሰሩ 2ሽህ ያህል ኢትዮጵያውያን የሚሰጠው የተሃድሶ ትምህርት ተጠናቆ ሰዎቹም መለቀቃቸውን ነው የመከላከያ ሚኒስትሩ ሲራጅ ፈጌሳ ለጋዜጠኞች የገለጹት።

የመንግት ኮሚኒኬሽንስ ጉዳዮች ጽ/ቤት ኃላፊ ሚኒስትር አቶ ጌታቸው ረዳ በአለፈው ሣምንት እንደተናገሩት ከሆነ እነዚህ የተሃድሶ ትምህርት ፕሮግራሞች፣ በብዛት የታሰሩትን ሰዎች በተመለከተ መንግሥትን በእጅጉ ጠቅመዋል።

ቪኦኤዋ ማርታ ቫንደር ውልፍ በአዲስ አበባ ቆይታዋ ለተቃዋሚ ደጋፊዎች ስለሚሰጠው ስለዚህ “ተሃድሶ” ከጄኔቭ ተከታዩን ዘግባለች።

ዝርዝሩን ከተያያዘው ድምፅ ያዳምጡ፡፡

XS
SM
MD
LG