በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የሕግ ጠበቃና የስደተኞች ጉዳይ አማካሪ አቶ ሼክስፒር ፈይሣ


የሕግ ጠበቃና የስደተኞች ጉዳይ አማካሪ አቶ ሼክስፒር ፈይሣ
የሕግ ጠበቃና የስደተኞች ጉዳይ አማካሪ አቶ ሼክስፒር ፈይሣ

በዛሬው የ ”ዲሞክራሲ በተግባር” ፕሮግራማችን የሕግ ጠበቃና የስደተኞች ጉዳይ አማካሪ አቶ ሼክስፒር ፈይሣ አነጋግረናል።

ባለፈው ሳምንት ዓርብ አሸባሪዎች በፓሪስ ጥቃት ካደረሱ በኋላ፥ የሦሪያ ስደተኞችን በመቀበል ጥያቄ ላይ በዩናይትድ ስቴትስ ከባድ የፖለቲካ ክርክር ተቀስቅሷል። ፕሬዘዳንት ባራክ ኦባማ ለአሥር ሺህ የሦሪያ ጥገኝነት አመልካቾች ፍቃድ ለመስጠት ያላቸው እቅድ ከበርካታ የሪፐብሊካን ፓርቲው ሕግ አርቃቂዎች ተቃውሞ ገጥሞታል። ዲሞክራቲክ ፓርቲው ግን አሜሪካ ምን ጊዜም ቢሆን በሯ ለሰተኞች ክፍት መሆን አለበት ሲል ይከራከራል።

የአውሮፓ ህብረትም አህጉሪቱን ያጥለቀለቁትን በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ፍልሰተኞች በ 28ቱ አባል ሀገሮች መካከል አከፋፍሎ ለማስፈር የነበረውን እቅድ ለጊዜው አስቁሟል።

እራሱን እስላማዊ መንግሥት ነኝ እያለ የሚጠራው ጽንፈኛ ቡድን አሁን በያዘው የሽብር ተግባር ከቀጠለ በወደፊት የፍልሰተኞች እድል ላይ ምን ተጽዕኖ ይኖረዋል? በተለይ ከአፍሪካ የሚሰደዱትን፥ የኤርትራ፥ የኢትዮጵያ፥ የሱማልያና ሱዳን ስደተኞችን ምን ያህል ይጎዳል? ተቀባይ ሀገሮች አሜሪካና ያውሮፓ ህብረትስ ምን ማድረግ ይችላሉ?

በዚህ ዙሪያ ባለሞያ አነጋግረናል። የሕግ ጠበቃና የስደተኞች ጉዳይ አማካሪ አቶ ሼክስፒር ፈይሣ ይሆናሉ እንግዳችን። ያነጋገራቸው ሰሎሞን ክፍሌ ነው፣ ዘገባውን የተያያዘውን ፋይል በመጫን ያዳምጡ።

የሕግ ጠበቃና የስደተኞች ጉዳይ አማካሪ አቶ ሼክስፒር ፈይሣ
please wait

No media source currently available

0:00 0:07:22 0:00

XS
SM
MD
LG