ቻይና፣ ሦስት አህጉራትን በመሠረተ ልማት ለማስተሳሰር የወጠነችው “የመቀነት እና መንገድማገናኛ ተነሣሽነት” (Belt and Road Initiative) 10ኛ ዓመቱን አስቆጥሯል፡፡
ፕሮጀክቱን አስመልክቶ፣ የሀገራት መሪዎች ፎረም በቤጂንግ ሲካሔድ፣ ባለፉት ዐሥር ዓመታት፣ ሀገራት ተነሣሽነቱን መሠረት አድርጎ ያገኙት የፋይናንስ ብድር፣ በርግጥ ዕድል ነው ወይስ ዕዳ የሚለው ጉዳይ ትኩረትን ስቧል፡፡
የአሜሪካ ድምፅም፣ የፕሮጀክቱ ተነሣሽነት፣ ለኢትዮጵያስ ምን አመጣላት? በረከትን ወይስ መዐትን? በሚል፣ ከጉዳዩ ጋራ በተያያዘ ጥናት ያደረጉ ባለሞያንና ምሁርን አነጋግሯል፡፡
ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።
መድረክ / ፎረም