በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በኢትዮጵያ ወቅታዊ ጉዳይ ላይ ውይይት


አቶ ያሬድ ኃይለማርያም
አቶ ያሬድ ኃይለማርያም

በባህርዳርና በአዲስ አበባ የ5ከፍተኛ የኢትዮጵያ ባለሥልጣናትን ህይወት የወሰደ አመፅ ተከትሎ የኢትዮጵያ መንግሥት ከ3መቶ በላይ ሰዎችን በተጠርጣሪነት በቁጥጥር ሥር አውሏል፡፡

ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ጄነራል ሰዓረ መኮንንና ሲጎበኙዋቸው ነበሩ የተባሉት ሜጄር ጄነራል ገዛዒ አበራ፣ በጠባቂያቸው እንደተገደሉ የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ዶ/ር አምባቸው መኮንን የርዕሰ መስተዳድሩ የአደረጃጀት ዘርፍ አማካሪ አቶ እዘዝ ዋሴና የክልሉ ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ አቶ ምግባሩ ከበደ፣ በክልሉ ፀጥታ ቢሮ ኃላፊ ብርጋዴል ጄነራል አሳምነው ፅጌ መሪነት ተካሂደ ባሉት መፈንቅለ መንግሥት ሙከራ መገደላቸውን ባለሥልጣናት አስታውቀዋል፡፡

ግድያውን ተከትሎ መቀመጫውን ስዊዘር ላንድ ጄኔቫ ያደረገ ስብስብ ለሰብዓዊ መብቶች በኢትዮጵያ የተባለ ድርጅት ዋና ዳይሬክተር አቶ ያሬድ ኃይለማርያም፤ አሁን ኢትዮጵያ ላለችበት የፖለቲካ ቀውስ አስተዋፅዖ አበርክተዋል ያሏቸውን ነጥቦች ለአንባቢ ያጋሩበትን ጽሁፍ በፌስቡክ አቅርበዋል፡፡ ጽሁፋቸው በዚህ በአለፈው አንድ ዓመት ለውጡን ለማሳለጥ ሊወሰዱ ይገባ ነበር ያሉትንና ወደፊትም መደረግ ስላለባቸው ጉዳዮች ፍንጭ የሚሰጥ ነው፡፡

የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።

በኢትዮጵያ ወቅታዊ ጉዳይ ላይ ውይይት
please wait

No media source currently available

0:00 0:33:02 0:00

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG