በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ኮሮናቫይረስ - በቻይና


ኮሮናቫይረስ የሚሉት አዲሱ ቫይረስ በተቀሰቀሰባት በቻይና አልፎም በሌሎች ሃገሮች ይዛመታል ተብሎ እየተጠበቀ ነው።

የዓለም የጤና ድርጅት ሌሎች ሃገሮችና መንግሥታት የቫይረሱን መዛመት ለመከላከል ሌሎች ሃገሮች እና መንግሥታት በጤና ተቋማት የመከላከል ዕርምጃዎች እንዲወስዱ ተማጽኗል።

በቫይረሱ የተጠቁ ሁለት መቶ ሰባ ስምንት ሰዎች መኖራቸውን እና ስድስት ሰው መሞቱን የዓለሙ የጤና ድርጅት አረጋግጧል።

የዓለም የጤና ድርጅት ኮሮና ቫይረስ ዓለምቀፍ ትኩረት የሚጠይቅ አጣዳፊ የህዝብ ጤና ጥበቃ ጉዳይ ይሁን፣ አይሁን ለማጤን ነገ አስቸኳይ ስብሰባ እንደሚያካሂድ አስታውቋል። ዓለምቀፍ ኤክስፐርቶች ያሉበት ቡድን ቫይረሱ ወደተቀሰቀሰባት ወደ ቻይና ዉሃን ከተማ ተጉዟል። የበሽታውን ምንጭ ለመረዳት ከከተማዋ የጤና ባለሥልጣናት እየሰሩ ናቸው።

የዓለም የጤና ድርጅት ቃል አቀባይ ታሬክ ጃሳሬቪክ ስለአዲሱ ኮሮናቫይረስ ብዙም የሚታወቅ ነገር እንደሌለ ገልጸው፣ በመሆኑም እንዴት እንደሚዛመት ህመሙ ምን ያህል ከባድ፣ ምን ያህል ተዛምቷል ምንጩስ ምንድነው የሚሉት ጥያቄዎች ግልጽ ያለ መልስ እስካሁን እንደሌለ ነው ያስረዱት።

ኮሮና ቫይረስ ለመጀመሪያ ጊዜ የተከሰተው በአለፈው የአውሮፓውያን ዓመት መጨረሻ ላይ ቻይናዋ ውሃን ከተማ የሚገኝ የአሳ ገባያ ላይ እንደሆነ ነው የተገለጸው።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG