በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ኢሶዴፓ ስለ ግጭቶቹ


በኦሮምያና በሶማሌ እንዲሁም በደቡብና በኦሮምያ አዋሣኝ አካባቢዎች ላይ እየታዩ ያሉት ግጭቶች ለሃገሪቱ አጠቃላይ የወደፊት ዕጣ አስጊ ናቸው ሲል የኢትዮጵያ ሶሻል ዴሞክራቲክ ፓርቲ አስጠንቅቋል።

በኦሮምያና በሶማሌ እንዲሁም በደቡብና በኦሮምያ አዋሣኝ አካባቢዎች ላይ እየታዩ ያሉት ግጭቶች ለሃገሪቱ አጠቃላይ የወደፊት ዕጣ አስጊ ናቸው ሲል የኢትዮጵያ ሶሻል ዴሞክራቲክ ፓርቲ አስጠንቅቋል።

ለሁኔታዎቹ አፋጣኝ መፍትሔ መስጠት እንዳለበት የጠየቁት የፓርቲው ምክትል ፕሬዚዳንት አቶ ጥላሁን እንደሻው ከቪኦኤ ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ ስለ ግጭቶቹ መፈጠር ፌደራሉ መንግሥታት በ“አንድ ለአምስት ጥርነፋ” ባሉትና “በሌሎችም የመረጃ መዋቅሮቹ እያወቀ ችላ ማለቱ ያስጠይቀዋል” ብለዋል።

የኢትዮጵያ ሶሻል ዴሞክራቲክ ፓርቲ ም/ሊቀመንበር አቶ ጥላሁን እንደሻው መረጃዎችን ከየአካባቢው እያሰባሰቡ መሆናቸውንም ገልፀው ለዚህ በሶማሌ - በኦሮምያ - በደቡብ ብሔር፣ ብሄረሰቦችና ሕዝቦች ክልሎች አዋሳኝ አካባቢዎች ላይ ለሚያይ ችግር መንግሥት ከምንም ነገር በላይ ቅድሚያና ትኩረት ሰጥቶ አፋጣኝ መፍትሄ እንዲፈለግ ፓርቲያቸው መጠዩቁን ተናግረዋል፡፡

አቶ ጥላሁን አንደሻው አክለውም ችግሮቹ ያሉት እራሱ ዘንድ መሆኑን መንግሥቱን ካመነ በካድሬዎቹና በታጣቂዎቹ ላይ የሚታይና ተጨባጭ እርምጃ መውሰዱ አንዳለበት ጠይቀው ከነድክመቱም ቢሆን የምናምነው መንግሥት አል ብለን ነውና ሆን ብሎ ካልሆነ ሕገ መንግሥቱን የሚጋፋ ታጣቂዎችንና አደረጃጀቱን ችላ ሊል አይገባም ብለዋል፡፡

ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።

ኢሶዴፓ ስለ ግጭቶቹ
please wait

No media source currently available

0:00 0:09:32 0:00

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG