በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ሚያዝያ ሃያ ሰባት - ብራና፣ የወርቆቹ ሣንቲሞችና ባንዲራው


አዲስ አበባ አራት ኪሎ የአርበኞች መታሰቢያ ሃውልት
አዲስ አበባ አራት ኪሎ የአርበኞች መታሰቢያ ሃውልት

ሰባ ስድስተኛው የድልና የነፃነት ቀን በመላ ኢትዮጵያ በዓለም ዙሪያ ባሉ ኢትዮጵያዊያንና የኢትዮጵያ ወዳጆች ዘንድ ተከብሮ ውሏል፡፡

ሰባ ስድስተኛው የድልና የነፃነት ቀን በመላ ኢትዮጵያ በዓለም ዙሪያ ባሉ ኢትዮጵያዊያንና የኢትዮጵያ ወዳጆች ዘንድ ተከብሮ ውሏል፡፡

አራት ኪሎ ላይ የሚገኘው የነፃነት ኃውልት መሠረት የተጣለው፤ አደባባዩም «የነፃነት አደባባይ» ተብሎ የተሰየመው ሚያዝያ 27/1935 ዓ.ም ልክ ከቀኑ አምስት ሰዓት ከአርባ አምስት ደቂቃ ላይ ነበር፡፡ ልክ የዛሬ ሰባ አራት ዓመት መሆኑ ነው፡፡

ቀዳማዊ ኃይለሥላሴ፤ ንጉሠ ነገሥት ዘኢትዮጵያ በዝግታ እርምጃ ወደ ኃውልቱ ጠጋ ብለው «በነበረው፤ በሚመጣውና በሚከተለው ትውልዶች ስም የሚመሠክሩ» ቅርሶችን በኃውልቱ መሠረት ውስጥ አኖሩ፡፡

በላዩ ላይ የተጣፈው በጊዜው ባይነገርም በነጭ ብራና ላይ የሠፈረ ፅሁፍ ከወርቅ ሣንቲሞች ጋር በኢትዮጵያ ሰንደቅ ዓላማ ተጠቅልሎ ሕዝቡ እያየ በመድፍ ቀለህ ውስጥ ተከተተ ...

በበርሜል ዓይነት ቅርፅ የተዘጋጀው ደንጊያ አምስት ሜትር ጥልቅ በሆነ ጉዳጓድ አናት ላይ እንደቆመ ሃምሣ አንድ ዓመት ዕድሜአቸው ላይ የነበሩት ንጉሠ ነገሥት ግዙፍ በሆነ ግርማ ወደ ኃውልቱ ተጠግተው «ለትውልድና ለዘመን ሁሉ ምሥክር ይሁን» ብለው ቅርሶቹ የገቡበትን በርሜል የማዕዘን ደንጊያ በዙሪያቸው ከነበሩ ጀግኖች ጋር ሆነው መሠረቱ ላይ አኖሩት ...

ንጉሤ አክሊሉ ሙሉውን ትረካ ይዟል፤ ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡

ሚያዝያ ሃያ ሰባት - ብራና፣ የወርቆቹ ሣንቲሞችና ባንዲራው
please wait

No media source currently available

0:00 0:06:34 0:00

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG