ዋሺንግተን ዲሲ —
የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፖብሊክ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሕመድ ያቀረቧቸውን አዳዲስ የካቢኔ አባላት ሹመት ዛሬ አፀደቀ።
እንዲሁም ከአዲሱ ካቢኔ በኢትዮጵያ ብሎም በአፍሪካ ለመጀመሪያ በሚባል ደረጃ 50 በመቶ ወይም ከ20 የካቢኔ አባላት ውስጥ አስሩ ሴቶች ናቸው።
ከቪኦኤ ጋር ቃለ ምልልስ ያደረጉት - በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፖብሊክ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የመንግሥት ረዳት ተጠሪ ሚኒስትር ደኤታ አቶ አማኑኤል አብርሃም የዛሬውን የካቢኔ ሹም ሽር ለየት የሚያደርገው ከአሁን በፊት የነበሩና ከዚህ በኋላ የማይቀጥሉ የሚኒስቴር መሥሪያ ቤቶች መኖራቸው ነው ብለዋል።
አዲሱ የካቢኔ አባላት የተመረጡትም በብቃት፣ በልምድ፣ በትምህርት ዝግጅት እና ለውጥን መምራት እንደሚችሉ ታምኖባቸው መሆኑንም አስረድተዋል። የነበሩት 28 የሚኒስቴር መሥሪያ ቤቶች ወደ 20 መቀነሳቸውም ለየት ያደርገዋል ብለዋል።
ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።
የፌስቡክ አስተያየት መስጫ