በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በሽብር ወንጀል ተጠርጥረው ታስረው የነበሩት ጦማሪያን እንዲፈቱ ትዕዛዝ ተላለፈ


 የዞን ዘጠኝ አምደኞችና ጋዜጠኞች
የዞን ዘጠኝ አምደኞችና ጋዜጠኞች

የኢትዮጲያ ፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በሽብር ወንጀል ተጠርጥረው ታስረው የነበሩትን ጦማርያን፣ ከሁለተኛው ተከሳሽ በስተቀር በነጻ እንዲፈቱ ትዕዛዝ አስተላልፏል።

በፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ዐሥራ ዘጠኛ ወንጀል ችሎት በሽብር ወንጀል ተከሰው ጉዳያቸው ለአንድ ዓመት ከአምስት ወር በላይ ሲታይ ከቆየው አምስቱ የዞን ዘጠኝ ጦማሪያን ወይም የኢንተርኔት አምደኞች አራቱ መከላከል ሳያስፈልጋቸው በዛሬው ዕለት በነጻ እንዲሰናበቱ ወሰነ፡፡ ሁለተኛውን ተከሳሽ በፍቃዱ ኃይሉን ግን በመደበኛው ወንጀል የወንጀል ድንጋጌ ‹‹እንዲከላከል›› ተወስኗል፡፡ በነጻ እንዲሰናበቱ የተወሰነላቸው ሦስቱ ጦማሪያን ማምሻውን ድረስ ከእስር አለመለቀቃቸው ታውቋል፡፡

ለስድስት ጊዜ ያህል ለውሳኔ ሲንከባለል የቆየው የጦማሪያኑ ጉዳይ በዛሬው ዕለት በችሎት ሲነበብ፤የፌደራል ዓቃቤ ሕግ በተጠርጣሪዎቹ ላይ ያቀረበው የድምጽና የሰነድ ማስረጃ የቀረበባቸውን የወንጀል ክስ ስለመፈጻማቸው አንዱም አያስረዳም ሲል ውሳኔ ሰጥቷል፡፡ በዚህም መሰረት በሌለችበት ተከሳ የነበረችው ሶሊያና ሽመልስ፣ናትናኤል ፈለቀ፣አቤል ዋበላና አጥናፉ ብርሃኔ በነጻ እንዲሰናበቱ ትዕዛዝ ሰጥቷል፡፡

የተከሳሾቹን ጉዳይ ከመጀመሪያ ጀምሮ የያዘው ጠበቃ አቶ አመሐ መኮንን፣የናትናኤል ፈለቀና አቤል ዋበላ ወላጆች ለዘጋቢያችን መለስካቸው አመሐ አስተያየታቸውን ሰጥተዋል፤ሙሉ ዘገባውን ከተያያዘው ድምጽ ያድምጡ፡፡

በሽብር ወንጀል ተጠርጥረው ታስረው የነበሩት ጦምሪያን እንዲፈቱ ትዕዛዝ ተላለፈ /ርዝመት - 6ደ 36ሰ/
please wait

No media source currently available

0:00 0:06:35 0:00

XS
SM
MD
LG