በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የኢትዮጵያ ይፋ በዓላት


የኢትዮጵያ ይፋ በዓላት
please wait

No media source currently available

0:00 0:05:50 0:00

የኢትዮጵያ ይፋ በዓላት

ኢትዮጵያ በዓመት ውስጥ አራት “ብሔራዊ” ተብለው የተጠሩና ስምንት ሃይማኖታዊ በዓላትን እንድታከብር የሚደነግግ ህግ ፓርላማው ዛሬ፤ ማክሰኞ አፅድቋል።

መስከረም አንድ የዘመን መለወጫ (እንቁጣጣሽ)፣ የካቲት 23 የዓድዋ ድል መታሰቢያ፣ ሚያዚያ 23 የዓለም የሠራተኞች (የላብአደሮች) ቀንና ሚያዚያ 27 የዐርበኞች (የድል) ቀን በዓላት ናቸው።

የሰማዕታት ቀን የካቲት 12፣ እንዲሁም የብሔር ብሔረሰቦች ቀን ኅዳር 29 ታስበው እንዲውሉ ተደንግጓል።

መስቀል፣ ገና ወይም የልደት በዓል፣ ጥምቀት፣ ስቅለት፣ ትንሣኤ (ፋሲካ)፣ ኢድ-አል አድሃ (አረፋ)፣ መውሊድ እና ኢድ-አል ፈጥር ስምንቱ በመላ ሃገሪቱ ተከብረው የሚውሉ የሃይማኖት በዓላት ናቸው።

ታስበው እንዲውሉ ከተወሰኑት በስተቀር በ“ብሔራዊ” እና በሃይማኖታዊ በዓላት ቀናት፣ የመንግሥትና መንግሥታዊ ያልሆኑ ተቋማት ለሕዝብ አገልግሎት ዝግ እንደሚሆኑ በዐዋጁ ተነግሯል።

የደርግ መንግሥት ከወደቀ አንስቶ ያለ አዋጅ ሲከበር የቆየው "ግንቦት ሃያ" በዛሬው ድንጋጌ ውስጥ አልተካተተም።

ከግማሽ ምዕት ዓመት በኋላ የወጣው አዲስ ዐዋጅ መደናገርን ያስወግዳል ብለው እንደሚያስቡ የህገ መንግሥትና ሕገ መንግሥት ጉዳዮች መምህርና ተመራማሪ አሮን ደጎል ለቪኦኤ ገልፀዋል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG