በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

እስረኞችን የመፍታትና ማዕከላዊን የመዝጋት ውሳኔው በአስቸኳይ ግልጽ እንዲደረግ ተጠይቋል

የኢትዮጵያ መንግሥት ለዘመናት ሲክደው የነበረውን የፖለቲካ እስረኞች አምኖ ለመፍታት መወሰኑ የሚያስደስት ነው ያሉ ከዚህ ቀደም ታስረው የተፈቱ ሦስት የኢንተርኔት አምደኞች፤ “ነገር ግን ጉዳዩ እንደተለመደው የፖለቲካ ማታለያ ሆኖ እንዳይቀር ውሳኔው ግልጽ ሊደረግና በሀገሪቱ ውስጥ ባሉ እስር ቤቶች በየትኛውም የፖለቲካ አመለካከታቸው የታሰሩ ሰዎች በአስቸኳይ ሊፈቱ” ይገባል ብለዋል።

“በውሳኔው ሁሉም እስረኛ የማይካተት ከሆነ ማዳፈንና ለማታለል መሞከር ነው”- በፍቃዱ ኃይሉ

“ማዕከላዊ መዘጋቱ ብቻ ሳይሆን የማሰቃየት ተግባሩ ነው መቆም ያለበት” ጌታቸው ሽፈራው

“የታሰረው ሕዝብ ነው መፈታት ያለበት” - ስዩም ተሾመ

“የማሰቃያ ተግባር የሚፈፀመው ማዕከላዊ ብቻ አይደለም ሁሉም እንዲዘጉ እንፈልጋለን” - አምነስቲ

እስረኞችን የመፍታትና ማዕከላዊን የመዝጋት ውሳኔው በአስቸኳይ ግልጽ እንዲደረግ ተጠይቋል
please wait

No media source currently available

0:00 0:11:41 0:00

የኢትዮጵያ መንግሥት ለዘመናት ሲክደው የነበረውን የፖለቲካ እስረኞች አምኖ ለመፍታት መወሰኑ የሚያስደስት ነው ያሉ ከዚህ ቀደም ታስረው የተፈቱ ሦስት የኢንተርኔት አምደኞች፤ “ነገር ግን ጉዳዩ እንደተለመደው የፖለቲካ ማታለያ ሆኖ እንዳይቀር ውሳኔው ግልጽ ሊደረግና በሀገሪቱ ውስጥ ባሉ እስር ቤቶች በየትኛውም የፖለቲካ አመለካከታቸው የታሰሩ ሰዎች በአስቸኳይ ሊፈቱ” ይገባል ብለዋል።

ከደርግ ሥርዓትም በኋላ ትውልድን በማምከን የሚታወቀው የማሰቃያ ቦታ “ማዕከላዊ” እስር ቤት እንዲዘጋ መወሰኑ የሚያስደስት እነደሆነ የገለጹት አምደኞቹ፤ “በዋናነት እርምጃ ሊወሰድበት የሚገባው ደግሞ የሰዎችን ሰብዓዊ መብት በጣሰ መልኩ ማሰቃየትና ማቆም ነው ምክንያቱም አሁን እነሸዋ ሮቢትም ሰው እየተሰቃየባቸው ስለሆነ” ብለዋል።

ዓለም አቀፉ የሰብዓዊ መብት ድርጅት አምነስቲ ኢንተርናሽናል እስረኞቹ መፈታታቸውም ሆነ እስር ቤቱ መዘጋቱ መልካም ነገር ቢሆንም “ያላለቁ ግን ብዙ ነገሮች አሉ” ሲል ለአሜሪካ ድምጽ ገልጿል።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG