በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በሰሜን አሜሪካ የስፖርት ፌደሬሽን በዓል በቶሮንቶ ተጀመረ


በሰሜን አሜሪካ የኢትዮጵያዊያን የስፖርትና ባሕል ፌዴሬሽን ፌደሬሽን /ኢኤስኤፍኤንኤ/ ሰላሣ ሦስተኛው ፌስቲቫል በካናዳዪቱ ቶሮንቶ ከተማ ዛሬ ተከፍቷል፡፡

please wait

No media source currently available

0:00 0:02:34 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ

በሰሜን አሜሪካ የኢትዮጵያዊያን የስፖርትና ባሕል ፌዴሬሽን ፌደሬሽን /ኢኤስኤፍኤንኤ/ ሰላሣ ሦስተኛው ፌስቲቫል በካናዳዪቱ ቶሮንቶ ከተማ ዛሬ ተከፍቷል፡፡

እስከ ፊታችን ቅዳሜ በሚዘልቀው የአንድ ሣምንት በዓል ላይ በሰሜን አሜሪካ የሚገኙ ኢትዮጵያዊያን በየሚኖበት አካባቢና ከተማ የተደራጁባቸው ሰላሣ ሁለት የእግር ኳስ ቡድኖች ለግጥሚያ እንደሚሰለፉ ታውቋል፡፡

በአለን ኤ. ላምፖር ስታዲየም በካናዳ ሰዓት ዛሬ ምሽት ላይ በተከፈተው ሥነ-ሥርዓት ላይ የፌዴሬሽኑ ፕሬዚዳንት ጌታቸው ተስፋዬ ንግግር አድርጓል፡፡

የዘንድሮው የፌዴሬሽኑ የክብር እንግዳ የቀድሞ የአንድነት ቡድን ተጫዋች አስቻለው ደሴ ነው፡፡

ESFNA-16-TORONTO OPENENG
ESFNA-16-TORONTO OPENENG

የፊታችን ዓርብ የኢትዮጵያ ቀን በሚል ሥያሜ የሚካሄዱ ክንዋኔዎች እንደሚስተናገዱና በማግሥቱ ቅዳሜ ለዋንጫ በሚደረግ ጨዋታ የሰላሣ ሦስተኛው በሰሜን አሜሪካ የኢትዮጵያ የስፖርት ፌደሬሽን ፌስቲቫል እንደሚዘጋ ታውቋል፡፡

ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡

XS
SM
MD
LG