በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የግብፅ እና የሶማሊያ መሪዎች ለሦስትዮሽ ጉባኤ አስመራ ናቸው


የሶማሊያ ፕሬዚደንት ሀሰን ሼክ መሀሙድ የግብፅ ፕሬዚደንት አብዱልፈታህ አል ሲሲየኤርትራ ፕሬዚደንት ኢሳያስ አፈወርቂ በአስመራ
የሶማሊያ ፕሬዚደንት ሀሰን ሼክ መሀሙድ የግብፅ ፕሬዚደንት አብዱልፈታህ አል ሲሲየኤርትራ ፕሬዚደንት ኢሳያስ አፈወርቂ በአስመራ

የኤርትራ፣ የግብፅ እና የሶማሊያ መሪዎች ዛሬ ሀሙስ በአስመራ የሦስትዮሽ የመሪዎች ጉባኤ እያካሄዱ ነው።

የግብፅ ፕሬዚደንት አብዱልፈታህ አል ሲሲ እና የሶማሊያ ፕሬዚደንት ሀሰን ሼክ መሀሙድ አስመራ የገቡት በኤርትራ ፕሬዚደንት ኢሳያስ አፈወርቂ ግብዣ ነው።

የኤርትራ የማስታወቂያ ሚኒስትር የማነ መስቀል “ጉባኤው በሦስቱ ሀገራት መካከል ያለውን ግንኙነት በማጠናከር፣ በቀጠናዊ ጸጥታ እና መረጋጋት ጉዳዮች ላይ ያተኮረ ነው” ብለዋል፡፡

የግብፁ መሪ ኤል-ሲሲ ከብሄራዊ ደህንነት ሚኒስትራቸው፣ ከካቢኔያቸው ዋና ኃላፊ፣ እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትራቸው ጋር እንደተገኙ የገለጹት አቶ የማነ፣ ልዑካኑ በፕሬዚደንት ኢሳያስ አፈወርቂ አቀባበል እንደተደረገላቸው ተናግረዋል፡፡

"ሁለቱ መሪዎች በነገው ዕለት የሁለትዮሽ ግንኙነታቸውን በማሻሻል እና በሌሎች የጋራ ጉዳዮች ላይ ይወያያሉ" ብለዋል።

የሶማሊያው ፕሬዚዳንት መሀሙድ አስመራ የደረሱት ከአንድ ቀን በፊት ቀደም ብለው ነበር፡፡

ፕሬዝዳንቱ ትላንት ረቡዕ አመሻሽ ላይ ከፕሬዝዳንት ኢሳያስ ጋር መወያየታቸውንና በሁለትዮሽ፣ ቀጠናዊ እና አለም አቀፍ የጋራ ጉዳዮች ዙሪያ ሰፊ ውይይት ማካሄዳቸውን አቶ የማነ ተናግረዋል።

የማስታወቂያ ሚኒስትሩ የማነ "ሁለቱ ሀገራት የሶማሊያን ሉዓላዊነት፣ የግዛት አንድነት፥ ነፃነት እና የሶማሊያን አንድነት በማስጠበቅ ረገድና ባለፉት አሰርት ዓመታት የእድገት መሰናክል ሆኖ የቆየውን ትልቅ ተግዳሮት በሚመለከት የእህትማማች ሀገራትን የሁለትዮሽ ትብብር የበለጠ ማጠናከራቸው አስፈላጊ መሆኑን ሁለቱ መሪዎች አስምረውበታል።” ሲሉ በኤክስ ማህበራዊ ገጽ መድረካቸው ላይ አስፍረዋል፡፡

"በዚህ አግባብ፣ ሁለቱ መሪዎች፣ ጠንካራ እና የበለጸገች ሀገር መገንባት ማለት፣ አስተማማኝ የመከላከያ እና የደህንነት መዋቅርን ጨምሮ ጠንካራ እና ሉዓላዊ ተቋማት መገንባት መሆኑን ተገንዝበዋል” ሲሉ የማነ አክለዋል፡፡

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG