በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የኤርትራ አየር መንገድ ወደ አዲስ አበባ በረራ ጀመረ


የኤርትራ አየር መንገድ ዛሬ ወደ አዲስ አበባ መብረር ጀምሯል።

የኤርትራ አየር መንገድ ዛሬ ወደ አዲስ አበባ በረራውን ጀምሯል።

130 ተሣፋሪዎችን ይዞ አዲስ አበባ በገባው በዛሬው የኤርትራ አየር መንገድ የመጀመሪያ በረራ የኤርትራ የትራንስፖርትና መገናሀኛ ሚኒስትር አቶ ብርሃነ ተስፋሥላሰ፣ የቱሪዝም ሚኒስትር ወ/ሮ አስካሉ መንቆርዮስ፣ የሃገሪቱ የሲቪል አቪየሽንና የአየር መንገዱ ከፍተኛ ኃላፊዎችም እንደሚገኙ ታውቋል።

የኤርትራ አየር መንገድ በሣምንት ሦስት ጊዜ፤ ሰኞ፣ ሐሙስና ቅዳሜ ከአሥመራ አዲስ አበባ እንደሚበር የአየር መንገዱ የንግድ ሥራ አስኪያጅ አቶ ገብረተንሣይ ጴጥሮስ ገልፀዋል።

በኤርትራ አየር መንገድ ከአሥመራ የሚሣፈሩ መንገደኞች አዲስ አበባን እንደመሸጋገሪያ ተጠቅመው በኢትዮጵያ አየር መገድ ወደሌሎች መድረሻዎች ለመጓዝ እንዲችሉ ከኢትዮጵያ አየር መንገድ ጋር መስማማታቸውን አቶ ገብረተንሣይ አመልክተዋል።

የኤርትራ አየር መንገድ በመጀመሪያ በረራው አዲስ አበባ ሲገባ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ ወ/ሮ ሂሩት ዘመነና ሌሎችም ባለስልጣናት አቀባበል አድርገውለታል።

"የሕዝብ-ለሕዝብ ቡድን" በተባሉ ተሣፋሪዎች ከኢትዮጵያ የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች የተውጣጡ 465 ሰዎችን ይዞ የበረራ መሥመሩ አገልግሎት ከተቋረጠ ከሃያ ዓመታት በኋላ የኢትዮጵያ አየር መንገድ እንደገና ለጀመረው በረራው ነሐሴ 11/2010 ዓ.ም. አዲስ አበባ መግባቱ ይታወሣል።

የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።

የኤርትራ አየር መንገድ ዛሬ ወደ አዲስ አበባ በረራውን ጀምሯል።
please wait

No media source currently available

0:00 0:01:32 0:00

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG