በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ለፀደቀው ዐዋጅ የተሰጠው ድምፅ አነጋጋሪ ሆኗል


የፓርላማው አባላት በአስቸኳይ ጊዜ ዐዋጁ ላይ ድምፅ ሲሰጡ
የፓርላማው አባላት በአስቸኳይ ጊዜ ዐዋጁ ላይ ድምፅ ሲሰጡ

በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የፀደቀው የአስቸኳይ ጊዜ ዐዋጅ አፀዳደቅ በሕገ መንግስቱ መሰረት ግድፈት አለበት ሲሉ ያነጋገርናቸው የፖለቲካ ፓርቲ አመራርና የሕግ ባለሞያ ገለፁ። በሀገሪቱ ሕገ መንግስት ላይ ዐዋጁ በሁለት ሦስተኛ ድምፅ መፅደቅ እንዳለበት በግልፅ እንደሚያስቀምጥና ይህ ድምፅ ደግሞ አለመገኘቱን ይናገራሉ።

በሚኒስትሮች ምክር ቤት የወጣውና ለኢትዮጵያ ፓርላማ ቀርቦ የፀደቀው ዐዋጅ የድምፅ ቆጥራ ሂደቱ አነጋጋሪ ሆኗል። በእንግሊዝ የኬል ዩኒቨርሲቲ በመምሕርነት የሚያገለግሉት ዶ/ር አወል አሎ፤ በአፈ ጉባኤ አቶ አባዱላ ገመዳ በተነገረውን የድምፅ ቆጠራ ውጤት መሰረት ዐዋጁ እንዳልፀደቀ ሕገመንግሥቱ ጠቅሰው ተናግረው ነበር።

ነገር ግን ምክር ቤቱ ቆይቶ በላከልን ማስተካከያ የቆጠራው ውጤት 346 ሳይሆን 395 ብሏል።

የአምቦ ዩኒቨርስቲ ወሊሶ ካምፓስ መምሕሩ ስዩም ተሾመና የኦፌኮው ምክትል ሊቀመንበር አቶ ሙላቱ ገመቹ ይህን አይቀበሉትም።

ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያድምጡ።

ለፀደቀው ዐዋጅ የተሰጠው ድምፅ አነጋጋሪ ሆኗል
please wait

No media source currently available

0:00 0:08:47 0:00

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG