በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የኢትዮጵያ ቡና አደጋ ላይ ነው


በመጭዎቹ የሰማንያ ዓመታት የጊዜ ጉዞ ውስጥ የኢትዮጵያ ቡና ከሚመረትበት አካባቢ ወደ ስድሣ ከመቶ የሚሆነው ክልል ለቡና ምርት የማይስማማ ሊሆን እንደሚችል ከትናንት በስተያ የወጣ አንድ የጥናት ሪፖርት አስጠንቅቋል፡፡

"ቡና፡- የሠለጠነው ዓለም ተመራጭ መጠጥ"

ቶማስ ጃፈርሰን - የዩናይትድ ስቴትስ መንግሥት መሥራች አባት፤ የአርነት አዋጅ ፀሐፊ፤ የዩናይትድ ስቴትስ ሦስተኛ ፕሬዚዳንት

በመጭዎቹ የሰማንያ ዓመታት የጊዜ ጉዞ ውስጥ የኢትዮጵያ ቡና ከሚመረትበት አካባቢ ወደ ስድሣ ከመቶ የሚሆነው ክልል ለቡና ምርት የማይስማማ ሊሆን እንደሚችል ከትናንት በስተያ የወጣ አንድ የጥናት ሪፖርት አስጠንቅቋል፡፡

ይህ ኔቸር ሪሰርች ወይም «የተፈጥሮ ምርምር» የሚባል ድርጅት በ«ኔቸር ፕላንትስ» ሕትመቱ ላይ ባወጣው ፅሁፍ በዓለም እጅግ ተወዳጅና ታዋቂም የሆነው «አራቢካ» እየተባለ የሚጠራው የኢትዮጵያ ውልድ የሆነ ቡና የሚያበቅለው አካባቢ በአየር ንብረት ለውጥ ምክንያት የመጎዳት ወይም የመጥፋት አደጋ ላይ መሆኑን አሳይቷል፡፡

ባራክ ኦባማ የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ሳሉ ኢትዮጵያን በጎበኙበት ወቅት ቡና ሲጠጡ
ባራክ ኦባማ የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ሳሉ ኢትዮጵያን በጎበኙበት ወቅት ቡና ሲጠጡ
"ባለፉ መቶዎች ዓመታት ውስጥ ኢትዮጵያ ለዓለም ከሰጠቻቸው በረከቶቿ መካከል አሜሪካዊያን ሁሉ ሊያመሠግኗችሁ እንደሚፈልጉ እርግጠኛ የሆንኩበት በተለይ አንድ ነገር በዓለም ዙሪያ ያሉ ሕዝቦችን እንዲሁም ዋይት ሃውስን ቀንና ሌሊት ቀጥ አድርጎ የያዘ ቡና ነው፡፡ ኢትዮጵያ እናመሠግንሻለን፡፡ ዋይት ሃውስ ውስጥ ግዙፍ የቡና ተጠቃሚዎች ነን፡፡"
ባራክ ኦባማ - የዩናይትድ ስቴትስ አርባ አራተኛ ፕሬዚዳንት

ጥናቱ የተካሄደው ለንደን የሚገኘው ኬው ሮያል ቦታኒካል ጋርደንስ ወይም የብዝኃ ዕፅዋት እንክብካቤና ምርምር ማዕከል ባልደረባ በሆኑት ዶ/ር አሮን ዴቪስና ጄስተን ሞት፤ እንዲሁም የኢትዮጵያው የተፈጥሮ አካባቢና የቡና ደን መድረክ ወይም በእንግሊዝኛ መጠሪያው ምኅፃር ‘ኢ.ሲ.ኤፍ.ኤፍ.’ ተብሎ በሚታወቀው ተቋም መሪ በዶ/ር ታደሰ ወልደማርያም ጎሌ ነው፡፡

ጃን ኬሪ የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሳሉ ኢትዮጵያን በጎበኙበት ወቅት ቡና ሲጋበዙ
ጃን ኬሪ የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሳሉ ኢትዮጵያን በጎበኙበት ወቅት ቡና ሲጋበዙ

ወፍ ዘራሽ ሆኖ በተፈጥሮ የበቀለውና ዛሬ በዓለም ዙሪያ በስፋት እየተመረተም፤ እየተወደደም ያለው የቡና ዘር (በሣይንሳዊ መጠሪያው ‘ኮፊ አራቢካ’ ይባላል) የኢትዮጵያ ዝናባማ ጫካዎች የተፈጥሮ ሃብት - የእነርሱ ብቻ - መሆኑን ዶ/ር ታደሰ ወልደማርያም የዛሬ 14 ዓመት አውጥተውት የነበረ አንድ ፅሁፍ ይናገራል፡፡

"ከቡና በፊት ዓለም ምንኛ መጥፎ ነበረች?!"
ካሴንድራ ክሌር (ጁዲት ረሜልት) - አሜሪካዊት ደራሲ

ቡና 15 ሚሊየን ለሚሆን ኢትዮጵያዊ ገበሬ የለት ተለት ሕይወቱ የቆመበት ሃብት ነው፡፡ ለኢትዮጵያ ደግሞ ከወጭ ንግድ ከምታገኘው ገቢ ሩብ ያህሉን የሚሸፍን ነው፡፡

ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡

የኢትዮጵያ ቡና አደጋ ላይ ነው
please wait

No media source currently available

0:00 0:08:05 0:00
"ራሴን ልግደል? ወይስ አንዲት ስኒ ቡና ትሰጡኛላችሁ?!!"
አልቤር ካሙ - ፈረንሣዊ ፈላስፋ፣ ፀሐፊና ጋዜጠኛ

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG