በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የምርጫ 2007 ውጤቶች እየወጡ ነው፤


Provisional result posted in Makmama polling station in Shone town shows huge lead for rulng EPRDF
Provisional result posted in Makmama polling station in Shone town shows huge lead for rulng EPRDF

በተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች እስካሁን በየጣቢያዎቹ ይፋ የተደረጉትን የምርጫ ውጤቶች ተከትሎ በአዲስ አበባ፥ አምቦና መቀሌ በአካል ተገኝተው አንዳንድ የምርጫ ጣቢያዎችን ተዘዋውረው የተመለከቱ ዘጋቢዎቻችን ያጠናቀሯቸውን ዘገባዎች ዝርዝር በተከታታይ እንደሚከተለው ቀርበዋል።

ትላንት በተካሄደዉ አገር አቀፍ ምርጫ በአዲስ አበባ ተመዝግቦ ከነበረው ቁጥሩ ወደ 1.5 ሚሊዮን ከሚጠጋ ሕዝብ 90 ከመቶ የሚሆነው ድምጽ መሰጠቱ ተገለጸ። በየዩኒቨርሲቲዎች የሚሰጠው ድምጽ ዛሬ ይጠናቀቃል፤ ተብሎ ይጠበቃል። ሆኖም አንዳንድ ተቃዋሚ ፓርቲዎች ግን የምርጫዉ ዉጤት ተስፋ ሰጪ አይደለም ይላሉ።

please wait

No media source currently available

0:00 0:03:44 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ

በአምቦና አካባቢዋ ምርጫ ጣቢያዎችም «የድምፅ ቆጠራው ተጠናቆ ጊዜያዊ ውጤቶችም በተዘጋጁ ሰሌዳዎች ላይ መለጠፋቸው ተገልጿል።

ገዢው ኦህዴድ «ሰላማዊና ዲሞክራሲያዊ ምርጫ ተካሂዷል» ሲል፣ ተቃዋሚው መድረክ ደግሞ ሂደቱን በጽኑ ይተቻል።

በሌላ በኩል ከዚያው ከአምቦ ዞን፣ የኦሮሚያ ፌዴራሊስት ኰንግረስ ፓርቲ ምክትል ጸሐፊና የሥራ አስፈጻሚ አባል አቶ ደጀኔ ጣፋ፣ ሁለት ሰዎች መሞታችን ገልጸውልናል። እነማናቸው? ማነው የገደላቸው? ለምን?

የወረዳው አስተዳዳሪ አቶ መገርሳ ጉርሜዋ በበኩላቸው ለክሱ መልስ ሰጥተዋል። ዝርዝሩን ከዚህ ያድምጡ፤

please wait

No media source currently available

0:00 0:03:11 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ

በመቀሌ ዓረና መድረክን የወከሉት አቶ ገብሩ አስራት ትላንት በተካሄደው አገራዊ ምርጫ ድምፃቸውን አለመስጠታቸውን ገለጡ።

የመራጮች ካርድ እየተሰጠ በነበረበት የጊዜ ሰሌዳ ውስጥ እንዲሰጠኝ ብጠይቅም የምርጫ ጣቢያው ”ካርድ ጨርሰናል፥ የለንም፤” የሚል መልስ ተሰጠኝ፤ ነው ያሉት አቶ ገብሩ።

የመቀሌው የዘስላሰ የምርጫ ጣቢያ አስተባባሪ አቶ አባተ ወልደገብርኤል በበኩላቸው በእርግጥ የምርጫ ካርድ እጥረት አጋጥሞን ነበር ሆኖም አቶ ገብሩ በአካል መጥተው አልጠየቁኝም ይላሉ።

please wait

No media source currently available

0:00 0:06:02 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ

XS
SM
MD
LG