በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ከደቡብ አፍሪካው ምርጫ የወጡ ቅድመ ውጤቶች ኤኤንሲ አብላጫ ድምጽ አለማግኘቱን ጠቆሙ


የደቡብ አፍሪካ የምርጫ ኮሚሽን ብሔራዊ ውጤቶች ኦፕሬሽን ማዕከል
የደቡብ አፍሪካ የምርጫ ኮሚሽን ብሔራዊ ውጤቶች ኦፕሬሽን ማዕከል

ትላንት ረቡዕ ደቡብ አፍሪካ ውስጥ ከተካሄደው አገር አቀፍ ምርጫ እስካሁን የተገኙት ውጤቶች እንደሚጠቁሙት ላለፉት ሠላሳ ዓመታት በፓርላማው አብላጫ መቀመጫ ይዞ የኖረው የአፍሪካ ብሔራዊ ኮንግሬስ የሚሳካለት አይመስልም፡፡ ይህ ከሆነ የአፓርታይድ ስርዓቱ ከተወገደ ወዲህ ከፍተኛው ለውጥ ይሆናል፡፡

እስካሁን ከ16 ከመቶው የምርጫ ጣቢያዎች በገቡት ቅድመ ውጤቶች መሠረት ኤኤንሲ 42 ነጥብ 6 ከመቶውን ድምጽ ያገኘ ሲሆን ዲሞክራሲያዊ ህብረት ፓርቲው 25 ነጥብ 8 ከመቶ ማርክሲስቱ የኢኮኖሚ ነጻነት ታጋዮች ፓርቲው 8 ነጥብ 5 ከመቶውን ማግኘታቸውን የምርጫ ኮሚሽኑ መረጃ ያመለክታል፡፡

የተሰጡት ድምጽች በሙሉ ተጠናቅቀው ሲወጡ እስካሁን ከተገኙት ቅድመ ውጤቶች ጋር ተመሳሳይ ከሆኑ ገዢው የአፍሪካ ብሐራዊ ኮንግሬስ ከአንድ ወይም ከአንድ በላይ ፓርቲዎች ጋር ጥምረት ለመመስረት ይገደዳል፡፡ ይህም በሚቀጥሉት ሳምንታት ወይም ወራት ከአሁን ቀደም ታይቶ የማያውቅ የፖለቲካ ትርምስ ሊያስከትል እንደሚችል ተመልክቷል፡፡

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG