በደቡብ አፍሪካ ለሰላሳ ዓመታት በገዢ ፓርቲነት የቆየው የአፍሪካ ብሔራዊ ኮንግረስ (ኤኤንሲ) የበላይነቱን ጠብቆ ይቆይ እንደሁ ዛሬ በሃገሪቱ በመካሄድ ላይ ያለው ምርጫ እንደሚወስን በመጠበቅ ላይ ነው።
ከአፓርታይድ አገዛዝ ወዲህ ወሳኝ እንደሆነ በሚነገርለት ምርጫ፣ 27 ሚሊዮን ሰዎች ለመምረጥ የተመዘገቡ ሲሆን፣ የተቃዋሚ ፓርቲዎች መገዳደር፣ የሥራ አጥ ቁጥር መጨመር፣ የወንጀል መበራከት እንዲሁም አዲሱ ትውልድ ከጥቂት ነጮች አገዛዝ ጋራ ለተደረገው ትግል ብዙም ሥፍራ የማይሰጠው በመሆኑ፣ ኤኤንሲ የበላይነቱን ላይጠብቅ ስለሚችል ከሌሎች ጋራ ሥልጣን እንዲጋራ ሊገደድ ይችላል ተብሏል።
ኤኤንሲ አሁንም ሃገሪቱን መምራት እንዲቀጥል ሰዎች እምነት እንደሚጥሉብን ጥርጥር የለኝም”
በድጋሚ ለመመረጥ ጥረት በማድረግ ላይ ያሉት ፕሬዝደንት ሰሪል ራማፎሳ ድምፅ ከሠጡ በኋላ ሲናገሩ፣ “ኤኤንሲ አሁንም ሃገሪቱን መምራት እንዲቀጥል ሰዎች እምነት እንደሚጥሉብን ጥርጥር የለኝም” ብለዋል።
‘ዲሞክራቲክ አላያንስ‘ የተሰኘው ዋናው ተቃዋሚ ፓርቲ መሪ የሆኑት ጃን ስቲንሁይሰን፣ በምርጫው የትኛውም ፓርቲ የበላይነት እንደማይዝ ተናግረዋል።
“በሰላሳ ዓመታት ውስጥ ለመጀመሪያ ጊዜ በደቡብ አፍሪካ ለውጥ እንዲመጣ መልካም አጋጣሚው ተፈጥሯል” ሲሉ ተደምጠዋል የተቃዋሚው መሪ።
መድረክ / ፎረም