እየተካሔደ ባለው የአሜሪካ ፕሬዚዳንታዊ የምርጫ ዘመቻ፣ የጦር መሣሪያን የመታጠቅ መብት ጉዳይ አሜሪካውያንን መከፋፋሉን ቀጥሏል።
ፕሬዚዳንት ባይደን፥ የጅምላ ጥቃት ሊፈጸምባቸው የሚችሉ መሣሪያዎች እንዲታገዱ ይፈልጋሉ። ተቀናቃናቸው ዶናልድ ትረምፕ ደግሞ፣ “ባይደን የጦር መሣሪያ ባለቤቶች፣ በሕገ መንግሥቱ የፈቀደላቸውን መብት አደጋ ላይ ጥለዋል፤” ሲሉ ይከሳሉ።
ፕሬዚዳንት ባይደን በጉዳዩ ላይ የተናገሩት፣ ልጃቸው ጆ ባይደን የአደገኛ ዕፅ ተጠቃሚ መኾናቸውን በመደበቅ መሣሪያ ገዝተው ታጥቀዋል፤ በሚል በቀረበባቸው ክስ፣ የጥፋተኛ ውሳኔ በተላለፈባቸው ቀን ነው።
መድረክ / ፎረም